የሰርቢያ ና የኮሶቮ ውዝግብ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 26 2003ማስታወቂያ
ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የኮሶቮን ጦርነት ለማስቆም ከ12 ዓመት በፊት ጣልቃ ቢገባም በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ ቢፈስም የጠጠገ የሚመስለው ቁስል በየጊዜው እንደገና የማመርቀዝ አዝማሚያ ማሳየቱ አልቀረም ። ሁለቱ አገራት በመካከላቸው ያለውን አለመግባባት በመፍታት መልካም ግንኙነት እንዲመሰርቱ ከዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በተለይም ከአውሮፓ ህብረት በኩል በሚደረግ ግፊት ከጥቂት ወራት በፊት መነጋገር ቢጀምሩም ውይይታቸው አንድም ፈር ሳይዝ አዲስ ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል ።
ሂሩት መለሰ
አርያም ተከሌ