የሰማያዊ ፓርቲ የምሥራቅ ጎጃም አስተባባሪ ግድያ
ረቡዕ፣ ሰኔ 10 2007ማስታወቂያ
ሰማያዊ ፓርቲ ስለ ፓርቲው የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተባባሪ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ግድያ ከፖሊስ ግልፅ መረጃ አለማግኘቱን አስታወቀ ። የፓርቲው ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ፖሊስ ጉዳዩን እየተከተታተለ መሆኑ ከማሳወቅ ውጭ ለፓርቲው ግልፅ መረጃ እንዳልሰጠ ለዶቼቬለ ተናግረዋል ። ከትናንት በስተያ የተገደለው ወጣት ሳሙኤል ከዚህ በፊት በፀጥታ ኃይሎች መደብደብና መታሰሩን የገለፁት የፓርቲው ሊቀመንበር ጉዳዩ ፖለቲካዊ አንድምታ እንዳለውም ገልጸዋል ።የደብረ ማርቆስ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ይበልጣል ደምሰው በበኩላቸው የሳሙኤል ገዳይ እጅ ከፍንጅ መያዙን ግድያውንም በገንዘብ መነሻነት መፈጸሙን መናገሩንና ጉዳዩም በመጣራት ላይ መሆኑን ለዶቼቬለ አስታውቀዋል ። ሁለቱን ወገኖች ያነጋገረው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ