የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 2 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ ሰማያዊ ፓርቲ በርካታ የብሔራዊ ምክር ቤት እና የፓርቲዉ አባላት በመንግሥት ፀጥታ ኃይላት መታሰራቸዉን አስታወቀ።የፓርቲዉ ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት ባለፈዉ ሳምንት የኢትዮጵያ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ካወጀ ወዲሕ የፓርቲዉን መሪዎች ጨምሮ ከታሰሩት አባላቱ መካከል እስካሁን ድረስ ፍርድ ቤት የቀረቡት አንዱ ብቻ ናቸዉ። የፓርቲዉ ብሄራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ይድነቃቸዉ ከበደ በስልክ እንደገለፁት አባላቱ የታሰሩበት ምክንያት በዉል አይታወቅም። ፀሐይ ጫኔ አቶ ይድነቃቸዉን አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች።
ፀሐይ ጫኔ
ነጋሽ መሐመድ