የሰማያዊ ፓርቲ መግለጫ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 24 2008ማስታወቂያ
የተቃዉሞ ፖለቲካ ፓርቲዉ፤ ሰማያዊ ፓርቲ የታሠሩ አባላቱ እስኪፈቱ ድረስ ሰላማዊ ትግሉን እንደሚቀጥል አስታወቀ ። የፓርቲው አመራር አባላት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በተለያዩ ከተሞች ውስጥ የታሰሩ አባሎቻቸው የሚፈፀምባቸውን በደል ዘርዝረው የሀገሪቱን የፍትህ ስርዓትም ነቅፈዋል። ፓርቲው በዛሬው መግለጫው በኢትዮጵያ የሕግ የበላይነት እንዲከበር በሚያካሂደው ትግል የፖለቲካ ፓርቲዎች ህዝቡና ዓለም ዓቀፍ ማህበረሰብ ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አስተላልፏል ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ