የሰማያዊ አመራር አባላት የፍርድ ቤት ችሎት
ረቡዕ፣ መስከረም 5 2008ማስታወቂያ
ፍርድ ቤቱ ድንበር አቋርጠው ወደ ግንቦት ሰባት ሊቀላቀሉ ሲሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸው የተገለፀው እነዚሁ ተከሳሾች ዛሬ ያቀረቡትን አቤቱታም አዳምጧል ። ተከሳሾቹ እነ ብርሃኑ በማረሚያ ቤት እርስ በእርሳችን እንዳንገናኝ እና ህክምና እንዳናገኝ ተከልክለናል ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል ።ጉዳዩን ያዳመጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 14ኛ የወንጀል ምድብ ችሎት ፤ይህ አስተዳደራዊ ችግር እንደሆነ በመጥቀስ የሚመለከታቸው ኃላፊዎች እንዲያስተካክሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል።
ዩሀንስ ገብረ እግዚአብሔር
ልደት አበበ
ሂሩት መለሰ