1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሰላም የኖቤል ሽልማት የሕጻናት ጉዳይ ተቆርቋሪዎች

ዓርብ፣ መስከረም 30 2007

የዘንድሮ የሰላም የኖቤል ሽልማት ለፓኪስታንና ህንድ የሕጻናት ጉዳይ ተቆርቋሪዎች ተሰጠ። ኦስሎ ኖርዊ የሚገኘዉ የኖቤል ሽልማት ኮሚቴ ዛሬ እንደለገለፀዉ ፓኪስታናዊትዋ ማላላ ይሱፍዛይ እና ህንዳዊዉ ካይላሽ ሳትያርቲ በፀረ -ሕጻናት እና ወጣት እንቅስቃሴ እንዲሁም ሕጻናት በሙሉ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ባደረጉት ትግል ለሽልማት በቅተዋል።

https://p.dw.com/p/1DTM4
Nobelpreis 2014 Friedensnobelpreis Malala Yousafzai und Kailash Satyarthi Kombo
ምስል picture-alliance/dpa

«የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ የ2014 የኖቤል የሰላም ሽልማት ስለወጣቶችና ሕጻናት ጭቆናና የሕጻናት የትምህርት መብት ለታገሉት ለካይላሽ ሳታይራቲ እና ማላላ ይሱፍዛይ እንዲሰጥ ወስኗል። ሕጻናት ወደትምህርት ቤት መሄድ አለባቸው። ለገንዘብ ማግኛ ሲባል ሊበዘበዙ አይገባም።»

ወጣት ሴቶች የትምህርት እድል እንዲያገኙ ከፍተኛ ትግል በማካሄድዋ የምትታወቀዉ የ17 ዓመትዋ ፓኪስታናዊት ማላላ በጎርጎሮሳዊዉ 2012 ዓ,ም ከጽንፈኛዉ ታሊባን ቡድን በደረሰባት ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ላይ መዉደቅዋ ይታወሳል። ሌላዉ የዘንድሮ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ የ60 ዓመቱ ህንዳዊ ካይላሽ ሳትያርቲ፤ የጋንዲን ትልቅ የመነሳሳት ኃይል መርሃቸዉ በማድረግ በሕጻናት ላይ የሚደረገዉን የጉልበት ብዝበዛ በመቃወም በርካታ የተቃዉሞና ሰላማዊ ሰልፎችን በማነሳሳታቸዉ ይታወቃሉ። 900 ሽህ ይሮ ሽልማትን እንደያዘ የተነገረለት የሰላም ኖቤል ሽልማት የፊታችን ታህሳስ 10፣ 2014 ዓ,ም ኖርዌ ስቶክሆልም ላይ ይሰጣል።

Nobelpreis 2014 Friedensnobelpreis Malala Yousafzai
ምስል Reuters/L. MacGregor

በሌላ በኩል ትናንት ሃሙስ ፈረንሳዊው ደራሲ ፓትሪክ ሞዲያኖ የ2014 ዓም የሥነ ጽሑፍ የኖቤል አሸናፊ መሆናቸው ተገለጸ። ስቶክሆልም የሚገኘው የስዊድኑ የካሮሊንስካ ተቋም እንዳስታወቀው፣ እስከዛሬ 30 መጽሓፍት ያወጡት የ69 ዓመቱ ሞዲያኖ የሰዎችን አስደማሚ እጣ የማቅረብ ልዩ ችሎታቸለአሸናፊነት አብቅቷቸዋል። ሞዲያኖይህንኑ880,000 ዩሮ የያዘውን እና እአአየፊታችን ታህሳስ 10፣ 2014 ዓም በስቶክሆልም የሚሰጠውን ሽልማት ያገኙ 15ኛው ፈረንሳዊ ደራሲ ናቸው።

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሰ