የሮማዉ ርዕሠ-ሊቀ ጳጳስ ጉብኝት በመካከለኛዉ ምሥራቅ
ዓርብ፣ ሚያዝያ 30 2001ማስታወቂያ
የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳት ቤኔዲክት 16ኛ መካከለኛዉ ምሥራቅን ለመጎብኘት ዛሬ አማን-ዮርዳኖስ ገብተዋል።የቫቲካን ባለሥልጣኖች እንደሚሉት የካቶሊኮቹ መንፈሳዊ አባት በአይሁድ፥ በክርስትና እና በእስልምና ሐይማኖቶች ቅዱስ ሥፍራዎች የሚያደርጉት ጉብኝት አለማ የሠላም፥ የእርቅና የፍቅር መልዕክትን ማስተላለፍ ነዉ።ይሁንና የየሩሳሌሙ ወኪላችን ዜናነሕ መኮንን እንደዘገበዉ ርዕሠ-ሊቃነ ጳጳሳቱ ከዚሕ ቀደም በሰጧቸዉ አስተያየቶችና በወሰዷቸዉ እርምጃዎች ምክንያት ጉብኝታቸዉን አረቦችም አይሁዶችም በጥሩ ስሜት የሚቀበሉት አይመስሉም።
ዜናነሕ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ