1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የርዕዮት ዓለሙ መፈታት

ሐሙስ፣ ሐምሌ 2 2007

ለአምስት ዓመታት በእስር የቆየችዉ የጋዜጣ አምደኛ ርዕዮት ዓለሙ ዛሬ መፈታቷ ተሰምቷል። የሽብር ተግባር በማሤር በሚል ክስ ተመሥርቶባት የነበረችዉ ርዕዮት 14ዓመት እስራት ተፈርዶባት በይግባኝ ወደአምስት ዓመት ዝቅ መደረጉ ይታወሳል። ።

https://p.dw.com/p/1Fw0o
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

[No title]

«አመክሮም አልሞላሽም፣ ይቅርታም አልጠየቅሽም፤ መፈቺያ ጊዜሽ ስላለፈ ፈተንሻል» ብለውኝ ነው የለቀቁኝ ያለችው ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ከወህኒ ቤት እንድትወጣ የተነገራት ባልጠበቀችበት ወቅት መሆኑን ገልጣለች። ወደፊት ጽሑፎችን ለንባብ ማቅረብ እንደምትገፋበት የገለጠችው ጋዜጠኛ ርዕዮትን እና እህቷን በማነጋገር የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገ/ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገ/ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ