1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የራድዮ አሰና የሳተላይት ሥርጭት መቋረጥ

ሐሙስ፣ የካቲት 26 2007

ራድዮ አሰና የተባለው ከለንደን የሚተላለፈው የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚ የራድዮ ጣቢያ የሳተላይት ሥርጭቱን ማቋረጡን አስታወቀ ። የጣቢያው መሥራችና ዋና አዘጋጅ አቶ አማኑኤል ኢያሱ የራድዮ አሰና የሳተላይት ሥርጭት የቆመው የገንዘብ ድጋፍ በመታጣቱ ነው ። ነው ብለዋል ። ጣቢያው ገንዘብ ካገኘ ግን የሳተላይት ሥርጭቱን የመቀጠል እቅድ አለው ።

https://p.dw.com/p/1EmIj
ምስል picture alliance/blickwinkel/Blinkcatcher

ራድዮ አሰና ላለፉት 6 ዓመት ከለንደን በዋነኛነት ወደ ኤርትራና አካባባቢዋ እንዲሁም ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ሃገራት ልዩ ልዩ ዝግጅቶችን የሚያስተላለፍ ጣቢያ ነው ። የጣቢያው መሥራችና ዋና አዘጋጅ አቶ አማኑኤል ኢያሱ ጣቢያው የግል ፕሬስ በሌለባትና የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ብቻ በሚደመጥባት ኤርትራ የተሟላ የመረጃ ምንጭ ሆኖ እንዲያገልግል ታስቦ የተቋቋመ መሆኑን ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።
ይህን ዓላማ ይዞ በአጭር ሞገድ በሳምንት ሰወስቴ-ለየ-አንድ ሰዓት፤ ሳምንቱን በሙሉ ለ24 ሰዓታት በሳተላይትና በድረገፅ ደግሞ በየቀኑ የአንድ ሰዓት ስርጭቱን ሲያስተላልፍ የቆየው ራድዮ አሰና ካለፈው እሁድ አንስቶ በሳተላይት ማስተላለፉን አቁሟል ። አቶ አማኑኤል እንደተናገሩት ምክንያቱ የገንዘብ እጦት ነው ።

የቀድሞ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባልደረባ የነበሩት አቶ አማኑ ኤል እንደሚሉት የራድዮ አሰና የሳተላይት ሥርጭት ብዙ አካባቢዎችን የሚያዳርስ ነበር ። በተለይ ኤርትራ ለሚገኙ አድማጮች የተለየ ጠቀሜታም ነበረው ።
ለጣቢያው ሳይሰለቹ የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርጉ የቆዩ ሰዎችን ደግሞ ደጋግሞ ማስቸገሩ ስለከበደን የሰተላይት ስርጭቱን ለማቋረጥ ተገደናል የሚሉት አቶ አማኑኤል የተጠናከረ ድጋፍ ከተገኘ ግን ስርጭቱ የማይቀጥልበት ምክንያት አይኖርም ይላሉ ።

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ