የሪቻርድ ፓንክረስት መፅሐፍ
ረቡዕ፣ ሐምሌ 24 2005ማስታወቂያ
ከኢትዮጵያ ታሪክ ወደ ግል ታሪክ።እዉቁ የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪና ፀሐፊ ፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት በእስተ-እርጅናም ቢሆን ወደ ራሳቸዉ ታሪክ ዞር ብለዋል።ኢትዮጵያን ግን ሙሉ በሙሉ አልተዉ-አትም።የሰማንያ-ሰባት ዓመቱ አንጋፋ የታሪክ ተመራማሪ ከባለቤታቸዉ ከሪታ ፓንክረስት ጋር ሆነዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሳለፉቱን በተለይም የወጣትነት ትዝታቸዉን የሚያወሳ መፅሐፍ አሳትመዉ ትናንት አስመርቀዋል። ሐምሳ ሰወስት ዓመታት ኢትዮጵያ የኖሩት ባልና ሚስቶች በእንግሊዝኛ «ኢትዮፕያን ሬሜነሳንስ ኧርሊይ ዴይስ» የሚል ርዕሥ የሰጡት መፅሐፍ ሁለቱም በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ለንደን ዉስጥ ተመርቋል።በለንደን ዩኒቨርስቲ በተዘጋጀዉ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በርካታ ኢትዮጵያዉያን ተገኝተዉ ነበር።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ሥነ-ሥርዓት ተከታትሎ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ