1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሪቻርድ ሆልብሩክ ዜና ዕረፍት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 5 2003

የዩኤስ አሜሪካ ልዩ የአፍጋኒስታን እና የፓኪስታን ልዑክ ሪቻርድ ሆልብሩክ ትናንት ማታ አረፉ።

https://p.dw.com/p/QYHM
ምስል picture-alliance/ dpa

የዩኤስ አስተዳደር ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፡ ሆልብሩክ ያረፉት ሀኪሞች የተሰነጠቀውን የደም ባምቧ ለመጠገን የሀያ ሰዓት የቀዶ ጥገና ካደረጉላቸው ከጥቂት ቀናት በኋላ ነበር። የስድሳ ዘጠኝ ዓመቱ ሆልብሩክ ባለፈው ዓርብ ድንገት ህሊናቸውን በሳቱ ጊዜ ነበር ወደ ሀኪም ቤት የተወሰዱት። የስድሳ ዘጠኝ ዓመቱ ሪቻርድ ሆልብሩክ ከአራት አሰርተ ዓመት በላይ በዲፕሎማቲክ ሙያ ያገለገሉ ፖለቲከኛ ነበሩ፤ አከራካሪ የነበሩት ዲፕሎማት በተለይ የሚታወቁት ሶስት ዓመት የቆየውን የቦዝንያ የርስ በርስ ጦርነት ያበቃውን የዴይተን የሰላም ውል በማደራደራቸው ነው።

ዛቢን ሚውለር

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ