የሩስያ ባህር ኃይል እና የዩክሬይን ስምምነት
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 20 2002ማስታወቂያ
በስምምነቱ መሰረት፡ በክሬሚያ አካባቢ በጥቁር ባህር የሚገኘው የሩስያ ባህር ኃይል በዚያ ቢያንስ ሀያ አምስት ዓመት እንዲቆይ ተወስኗል። በምላሹ ክስረት አፋፍ ላይ የምትገኘዋ ዩክሬይን ከሩስያ በምትገዛው ጋዝ ላይ ሰላሳ ከመቶ ቅናሽ ታገኛለች። ስምምነቱን የተቃወሙት የዩክሬይን ምክር ቤት እንደራሴዎች በድምጽ አሰጣጡ ወቅት ሲሰዳደቡ፡ በእንቁላል ሲደባደቡ እና በጢስ ቦምብ ሲታጠኑ ታይተዋል።
አርያም ተክሌ
ተክሌ የኋላ