የሥልጣን ሽግግር ታሪክ በኢትዮጵያ፣
እሑድ፣ ግንቦት 15 2002ከማካሄዷ በስተቀር፣ በተለይ መሃል ግዛቷን አንድም የውጭ ኃይል ተቆጣጥሮት አያውቅም።
ሰፊውን ግዛቷን፣ ነግሥታት ፣ መሣፍንት፣ ሡልጣኖች፣ አሚሮች ተከፋፍልው ቢገዙም፣ አብዛኛውን ጊዜ በአንድ ማዕከላዊ አገዛዝ ሥር የኖረች ሀገር ናት።
ኢትዮጵያ ፣ የዘመኑ ሥልጣኔና አስተዳደር መዓዛ ከሸተታት፤ ከአንድ መቶ ዓመት በላይ አስቆጥሯል። ያም ሆኖ፣ የተለያየ ስያሜ ይሰጠው እንጂ፣ የአስተዳደር ስልቱ መሠረታዊ ለውጥ አልታየበትም። ኢትዮጵያውያን ፣ እንደ ንብረት ውርስ፣ በትውልድ ሥልጣን በሚተላለፍለት ግለሰብ፣ በሚሾም፣ ወይም በጉልበት ሥልጣን በሚጨብጥ መሪ መገዛት እንጂ፣ ህዝብ፣ በትክክል በሚመርጠው መሪ፣ የመተዳደር ዕድል አጋጥሞአቸው አያውቅም። በታሪኳ፣ በብዙ ጉዳዮች፣ ቀዳሚውን ቦታ የያዘችው ሀገር፣ በዚህ ረገድ በመጨረሻው ረድፍ ከተሰለፉት መካከል ሆኗል የምትደመረው።
በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ፣ የባዕድን ተጽእኖ የመከላከል የነጻነት ታሪክ፣ በህዝብ የሚመረጥ መንግሥት ለመመሥረት ያደጋተበት ምክንያት ምንድን ነው? በዩናይትድ እስቴትስ፣ ቨርጅኒያ ውስጥ፣ የክሪስቶፈር ንው ፖርት ዩኒቨርስቲ የታሪክ መምህር፣ ዶ/ር ሹመት ሲሻኝ፤
(ድምፅ)---------------
በምዕራቡ ዓለም እንደሚታየው ለቡድን ነጻነት መሠረት የሆነውን ፣ የግለሰቦችን ነጻነት ያጎናጸፈውን ፤ መሠረታዊ የዴሞካራሲ ሥርዓት ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመትከል ማን ያህል ጊዜ ይወስድ ይሆን?!
------(ዶ/ር ሹመት ሲሻኝ)---
ምርጫ 1997
የምዕራቡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት በአብዛኛው አለም በተንሠረፋበት በቅርቡ ዘመንም ኢትዮጵያውያን በፍላጎታቸው መሪዎቻቸውን ለመምረጥ ሞክረው ነበር ።
ከዚህ ቀደም ከተደረጉት ሶስት ሙከራዎች በአንፃራዊ መመዘኛ የተሻለው የ 1997 ምርጫ ነበር ። ውጤቱና መዘዙ ግን የነበረውን ተስፋ ሁሉ አጨናጉሎታል ። መሳይ መኮንን የዚያን ጊዜውን እውነታ በአጭሩ ይቃኘዋል ።
ተክሌ የኋላ
መሳይ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ