የሠብአዊ መብት ሕግና ገቢራዊነቱ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 30 2001ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል ሐገራት ታሕሳስ 1941 ያፀደቁት አለም አቀፍ ደንብ እስከዚያ ጊዜ በነበረዉ አለም አምባገነኖች ይፈፅሙት የነበረዉን ኢ-ሰብአዊ እርምጃ ለማስቆም የመጀመሪያዉ ዉሳኔ ነበር-የሆነዉ።ፓሪስ -ፈረንሳይ ተስይሞ የነበረዉ የአለም አቀፉ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ያፀደቀዉ አጠቃላይ የሰብአዊ መብት ደንብ የጀርመን ናትሴዎች በአዉሮጳ አይሁዶች ላይ ለፈፀሙት ግፍ፥ ሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ላደረሰዉ ጥፋት መልስ፥ ለሰዉ ልጅ መብት መከበር ደግሞ ፅኑ መሰረት ነዉ።ሕጉ የፀደቀበት ሥልሳኛ አመት ዘንድሮ ሲታሰብ ገቢራዊነቱ ዛሬም ማጠያየቁ ነዉ ጭንቁ።ኡልሪከ ማስት-ኪርሽኒንግ የዘገበችዉን ነጋሽ መሐመድ አጠናቅሮታል።