የሠርግ ድግስ ቅንጦትና ድህነት
ሐሙስ፣ ግንቦት 29 2005ማስታወቂያ
ሰርገኞች ተፈቃቅደዉ ሰርጋችንን በዚህ ወጭ እንሸፍን ብለዉ መጀመርያ ካሰቡበት የሂሳብ ድምር ፤ ወደ ኋላ በአምስት፤ ስድስት እጥፍ ወጭን እንዳወጡ ራሳቸዉ ሙሽሮቹ ይናገራሉ፤ ግን ለምን አስፈለገ? የኑሮ ዉድነት ከዕለት ወደ ዕለት መናሩ በሚነገርለት በሀገር ኢትዮጵያ የሚታየዉ የሰርግ ድግስ ወጭ ቅጥ ያጣ ነዉ የሚመስለዉ! ፉክክር ወይስ እዉን ይህን መሰል ድግስ አስፈልጎ?
ሰሞኑን የሰርግ መሰረግያ ወር ነዉና በሶስት ጉልቻ የጎለታችሁ በቃልኪዳን የተሣሠራችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ እንላለን፤ በቅድምያ! ግን የሰርግ ድግሳችሁ ምን ይመስል ነበር?ወጫችሁስ? በለቱ ዝግጅታችን፤ በአገራችን በተለይ በመዲናይቱ አዲስ አበባ የሰርግ ድግስን ብትመለከቱ ድህነትና ቅንጦትን በጉልህ ያለመነፅር መቃኘት ትችላላችሁ፤ የሚታየዉ ድግስ ከአቅማችን በላይ፤ እና አላስፈላጊ ነዉ የሚሉንን ባለሞያዎች ይዘን በኢትዮጵያ ባህላዊ የሰርግ አከባበርን እንቃኛለን፤ ሙሉዉን ዝግጅት ከጽሑፉ ስር የሚገኘዉን ማድመጫ ተጭነዉ ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ