1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሠለጠነ የሰው ጉልበት ብኩንነት፧

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 2 1996
https://p.dw.com/p/E0lE

በአፍሪቃ ክፍለ=ዓለም፧ በሙያ የሠለጠኑና በቀለም ትምህርትም የገፉበዛ ያሉ ስደተኞችን የምታስተናግድ ሀገር፧ ደቡብ አፍሪቃ ናት። ይሁንና፧ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽንና የጃፓን ዓለም-አቀፍ የትብብር ድርጅት ጥናት እንደሚጠቁመው፧ የተጠቀሱት ስደተኞች የሙያ ችሎታና ተመክሮ ጥቅም እንዲሰጥ አልተደረገም። በደቡብ አፍሪቃ ከሚገኙት ፺ ሺ ስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች መካከል ሲሦው፧ መደበኛ የ፩ኛ ደረጃ፧ 2/3ኛውም የ፪ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያገባደዱም ሆኑ ያጠናቀቁ ናቸው። ወደ ደቡብ አፍሪቃ ከመኮብለላቸው በፊት፧ ብዙዎቹ በልዩ ልዩ የሙያ ዘርፎች የተሠማሩ እንደነበሩ ጥናቱ ያመለክታል። ይኸው ጥናት እንደሚያስረዳው፧ በጆሃንስበርግ በኬፕታውን፧ በደርባንና በፕሪቶሪያ፧ የአጠቃላዩን የስደተኞች ኑሮ ለመገንዘብ ያስችላሉ ተብለው በተመረጡ 1,500 ሰዎች ነበር፧ ፪ ዓመት የወሰደው ምርምር ያተኮረው። ስደተኞቹ፧ የአንጎላ፧ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ፧ የሶማልያ፧ የኮንጎ ብራዛቪል፧ የቡሩንዲ፧ የሩዋንዳ፧ የኢትዮጵያ፧ የዩጋንዳ፧ የሴራሊዮን፧ የሱዳን፧ የላይቤሪያና የካሜሩን ተወላጆች ናቸው። ትውልድ ሀገርን ሳይወዱ መልቀቅ ግድ የሆነባቸው ስደተኞች፧ በተጠለሉበት ሀገር ክብራቸውየቱን ያህል ይጠበቃል? ደህንነታቸው የቱን ያህል አስተማማኝ ነው? የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ተጠሪ ቤማ ዶንኮ፧ እንደሚሉት፧ ለመጀመሪያ ጊዜ ሥርዓት ባለው መልክ የተካሄደው ጥናት ዓላማ፧ ይህንና የመሳሰለውን መርምሮ፧ መላ ለመሻት ነው። የደቡብ አፍሪቃ መንግሥትና ድርጅታቸው፧ በጥናቱ ውጤት በመመርኮዥ፧ በጋራ ውጤታማ የሆነ ተግባር ማከናወን ይችላሉ። የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ግን እስካሁን፧ የስደተኞቹን ችሎታ አልተጠቀመበትም። ዕድሉ ከተሰጣቸው ግን፧ ዶንኮ እንዳብራሩት፧ አብዛኞቹ የተማሩትና በሙያ የወለጠኑት ስደተኞች፧ ለደቡብ አፍሪቃ ብልፅግና የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ማበርከት አይሳናቸውም። ይሁንና በእንዲህ ዓይነት የግንባታ ተግባር ሊሠማሩ ቀርቶ፧ አብዛኞቹ ለህልውናቸው ሲጨነቁ፧ ሲጠበቡ ነው የሚታዩት። 44% ው ስደተኞች በቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነው የሚመገቡት። 21% ው ደግሞ፧ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አንዳንድ ጊዜ፧ የሚላስ-የሚቀመስ ሳያገኙ ነው፧ ውለው-የሚያድሩት። በደቡብ አፍሪቃ የሚኖሩ ስደተኞች፧ የቤተሰብ የወር ገቢአቸው 650 ራንድ(100 ዶላር) ነው። ፫ ከመቶው ምንም ዓይነት ገቢ የላቸውም። ጥናቱ እንደሚያመለክተው፧ 1/5ኛው ደቡብ አፍሪቃ ለመግባት፧ ነጻ መሆን ሲገባው ገንዘብ እንዲከፍሉ ተገደዋል። 17% ው የህክም