1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ በ36ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች

ሰኞ፣ ኅዳር 11 2010

ባለፉት አስር አመታት በአብዛኛው የአፍሪቃ አገሮች የመልካም አስተዳደር ሁኔታ መሻሻል ቢያሳይም መሻሻሉ ባለፉት አምስት አመታት የተጓተተበት፣ የተቀለበሰበት እና የቀነሰበትም አልጠፋም። ይኸን የሚለው ዛሬ ይፋ የተደረገው የሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን አመታዊ የመልካም አስተዳደር ዘገባ ነው።

https://p.dw.com/p/2nxPH
Logo der Mo Ibrahim Foundation

የሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን አመታዊ ዘገባ

በዘገባው መሰረት በኢትዮጵያ የህግ የበላይነት ባለፉት አምስት አመታት መሻሻል (+1.10) አሳይቷል። የግለሰቦች ደኅንነት (-3.15) እና ብሔራዊ ደኅንነት (-1.55) ግን ማሽቆልቆል ታይቶባቸዋል። የአፍሪቃ አገራት የ2016 ዓ.ም. የመልካም አስተዳደር ይዞታን የፈተሸው ዘገባ ለኢትዮጵያ በአጠቃላይ 47.7 ነጥብ ሰጥቷታል። ከአፍሪቃ አገራትም በ36ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ሞ ኢብራሒም ዛሬ ይፋ ስለተደረገው አመታዊ ዘገባ ለዶይቼ ቬለ "ተጨባጭ ምሥል ለመስጠት ሞክረናል። በተጨባጭ ምስል ውስጥ ደግሞ ጠባሳዎች እና ውብ ነቁጦች ይኖራሉ። እዚህ ጋ አንድ ነገር ማንሳት እፈልጋለሁ። የመልካም አስተዳደር በአጠቃላይ መሻሻል አሳይቷል። ይኸ አዎንታዊ ነገር ነው። የገጠሩ ዘርፍ የከፋ ውድቀት ውስጥ ባይገባም መሻሻል አላየንም። እጅግ ወሳኝ ነው ብለን ያየንው የወጣቶች ጉዳይ ነው። በአፍሪቃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወጣት ይገኛል። ለእነዚህ ወጣቶች ሥራ ማግኘት ይኖርብናል። የትምህርት እና የሥልጠና ጥራቱ መሻሻል ይገባዋል። በዚህ ረገድ ደስተኛ አይደለንም።" ብለው ነበር። 
በሱዳናዊው ባለጠጋ የተመሰረተው ሞ ኢብራሒም ፋውንዴሽን የአገራትን የመልካም አስተዳደር ሁኔታ የሚፈትሽበት ዘገባ ይፋ የሆነው ዛሬ ነው።

ድልነሳ ጌታነህ 

እሸቴ በቀለ

አርያም ተክሌ