የሞሪታንያ ተቀናቃኝ ወገኖችና ስምምነታቸው29 ግንቦት 2001ቅዳሜ፣ ግንቦት 29 2001ሞሪታኒያ ወታደራዊ መፈንቅለ-መንግሥት መሪዎች እና የተቃውሞ ወገኖች ሀገራቸው የምትገኝበትን ቀውስ ለማብቃት የሚያስችላቸው አንድ ስምምነት ከሁለት ቀናት በፊት ተፈራረሙ።https://p.dw.com/p/I4BWምስል picture-alliance/ dpaማስታወቂያመፈንቅለ መንግስት በተካሄደባት በምዕራብ አፍሪቃዊቱ ሀገር ሞሪታንያ በቁም እስር የቆዩት ጠቅላይ ሚንስትር ያህያ ዑልድ አህመድ ዋኬፍም ተፈተዋል። በሴኔጋል ዋና ሚና ተጫዋችነትና በዓለም አቀፍ ሸምጋዮች አደራዳሪነት የተደረሰው ስምምነት በሴኔጋል መዲና ዳካር ነበር የተፈረመው። AA/DW