1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ ዕጥረት በዚምባብዌ ዕስር ቤቶች

ረቡዕ፣ ሰኔ 3 2001

ምጣኔ ሀብቷ እጅግ በደቀቀው በዚምባብዌ ዕስር ቤቶች የምግብ ና፣ የውሀ ዕጦት እንዲሁም የንፅህና ጉድለት እጅጉን ተባብሷል ።

https://p.dw.com/p/I70u
ምስል AP

በዕስር ቤቶች በምግብ ማጣት እና በኤች.አይ.ቪ ኤድስ ያለቀውና የሚያልቀው ዕስረኛ ብዛት ጥቂት የሚባል አይደለም ። ይህን አሳዛኝ የዕስረኞች አያያዝ ለመለወጥ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶችና በጎ ፈቃደኞች የበኩላቸውን ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው ። በዚህ ተግባር ከተሰማሩት ውስጥ አንዱ የዓለም ቀይ መስቀል ድርጅት ሲሆን የዚምባብዌ ታራሚዎችን ለመርዳት በግል የሚንቀሳቀሱ በጎ አድራጊዎችም አልጠፉም ። ከነዚህም መካከል ሐራሬ ውስጥ ባለፈው ዓርብ ለዕሰረኞቹ ዕርዳታ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ያካሄዱት ኢትዮጵያውያንና ጀርመናውያን ይገኙበታል ።

ሂሩት መለሰ/ሸዋዬ ለገሠ