1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምግብ እጥረት፣ የስንዴ ግዢ እና ክፍፍል

ሰኞ፣ ኅዳር 13 2008

ባለፈዉ ሳምንት ኢትዮጵያ ለምግብ እጥረት ተጋለጡ ወገኖች የሚከፋፈል አንድ ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ መግዛቷ አንድ የመንግሥት ባለስልጣን ማስታወቃቸዉን ሮይተርስ መዘገቡ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/1HAwJ
Deutschland Kornkreise bei Berlin - Weißzenfeld
ምስል DW/D. Keating

[No title]

በዘገባዉ መሠረት፣ በድርቅ ምክንያት የተከሰተዉን ከፍተኛ የምግብ እጥረት ለመቋቋም ተጨማሪ አንድ ሚሊዮን ቶን ስንዴ ለመግዛትም ጨረታ ይወጣል። ባለፈዉ በልግ እና የክረምት ወራት ባጋጠመዉ የዝናብ እጥረት በአፍሪቃ ቀንድ በምትገኘዉ ሀገር በኢትዮጵያ የምግብ እና የዉኃ እጥረት ማስከተሉ ይታወቃል። ይህን ድርቅና የምግብ እጥረት ለመቋቋም እስካሁን 280 ሚሊየን ዶላር ወጭ መሆኑ ነዉ ከኢትዮጵያ መንግሥት የተሰማዉ። እንደ መንግስታቱ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልገዉ ሕዝብ ቁጥር እስከመጪዉ ጥር ወር ድረስ 15 ሚሊየን ሊደርስ እንደሚችል ተጠቅሶአል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጉስ በግብርና ሚኒስቴር የአደጋ መከላከልና ዝግጁነትና የምግብ ዋስትና ዘርፍ ሚኒስትር ዴታ አቶ ምትኩ ካሳን አነጋግርሮ ዘገባ ልኮልናል።

ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ