የምግብ ሳይንስ ባለሞያው ዶክተር አየለ ጉግሳ
ማክሰኞ፣ ጥቅምት 26 2006ማስታወቂያ
የማስትሬት ዲግሪያቸውን ከአሌክሳንደር ሁምቦልት ዩኒቨርስቲ ካገኙ በኋላ የዶክትሬት ዲግሪያቸው እዚያው ማጥናት ቀጥለው ሁለቱ ጀርመኖች ሲዋሃዱ ዩኒቨርስቲው የሚያጠኑትን ትምህርት መስጠት በማቋረጡ ወደ በርሊኑ የቴክኒክ ዩኒቨርስቲ ተዛውረው ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ በቅተዋል ። የዶክተር አየለ የማስትሬትና የዶክትሬት ዲግሪዎቻቸው የመመረቂያ ሥራዎች በተመሳሳይ መስክ ላይ ያተኮሩ ናቸው ።ዶክተር አየለ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ባገኙበት በበርሊኑ የቴክኒክ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለአራት ዓመታት በጥናትና ምርምር ሠርተዋል ። ከዚያ በኋላም በአንድ የዱቄት ፋብሪካ ውስጥ ተቀጥረው ያገለግሉም ነበር ። ለአምስት ዓመታት በዚሁ ፋብሪካ ውስጥ ያገለገሉት ዶክተር አየለ ከሁለት ዓመት ግድም ወዲህ ደግሞ በሙያቸው በግል ሥራ ላይ ይገኛሉ ። እውቀታቸውን ወደ ኢትዮጵያ በማሸጋገርም እየሰሩ ነው ። በዶክተር አየለ እምነት ኢትዮጵያን በመሰለች ሃገር ምግብ ማምረት አስቸጋሪ ባልሆነም ነበር ። ይሁንና በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ሃገሪቱ ከምግብ እጥረት ልትላቀቅ አልቻለችም ። ለዶክተር አየለ በኢትዮጵያ የምግብ እጥረት ሁለት ገፅታ አለው ።
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ