የምግባ መርሃ ግብር በትምህርት ቤቶች
ረቡዕ፣ ግንቦት 8 2004ማስታወቂያ
መንግሥት የትምህርት ቤቶች የምግብ መርሃ ግብርን እንደ አንድ የልማት መርህ አቅጣጫ እንዲይዝ ተጠየቀ ። ከዓለም ዙሪያ የተሰበሰቡ ከ 200 በላይ የሚሆኑ የመስኩ ባለሞያዎችና የሚመለከታቸው አካላት የተገኙበት አዲስ አበባ ውስጥ የተካሄደ ጉባኤ የትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃ ግብር ለማህበረሰቡና ለአነስተኛው ገበሬ የልማት አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው አሳስቧል ። በጉባኤው የምግብ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች በትምህርት ቤቶች የሚካሄደው የምገባ መርሃ ግብር ወጥነትና የመንግሥት ተሳትፎ ወሳኝ መሆናቸው ተነግሯል ። በጉባኤው ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ታደሰ እንግዳው ዝርዝሩን ልኮልናል ።
ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ