የምድር ባቡር ሠራተኞች ቅሬታ
ዓርብ፣ መስከረም 24 2006ማስታወቂያ
አንዳንድ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የምድር ባቡር ኩባኒያ የቀን ሰራተኖች ለዶቸቬሌ እንደገለጹት በእለት ክፍያ ኣከፋፈል ለያ በደል እየደረሰባቸው ነው። በሌላ ቦታ በተመሳሳይ የቀን ስራ ላይ የተሰማሩ የኩባኒያው ሰራተኖች እንደየ ስራ መደባቸው በቀን ከ50 እስከ 100 ብር ይከፈላቸዋል። እነሱ ግን ሰራተኖቹ እንደሚሉት ከ25 እስከ35 ብር ብቻ እየተከፈላቸው ነው። ይህንኑ ገልጸው ለአለቆቻቸው ቅሬታ ቢያቀርቡም ሰሚ ኣላገኙም ። እንዲያውም በዚሁ መሰረት የማትሰሩ ካልሆነ ከስራ ትባረራላችሁ የሚል ማስጠንቀቂያ ተሰቶናል ሲሉም ያማርራሉ። ጥያቄያቸውን ለሚመለከተው የኩባኒያው ወይንም የመንግስት አካል ኣቅርበው ለመሙዋገትም ኣቅሙም ሆነ እድሉም እንደሌላቸው የገለጹት እነዚሁ የምድር ባቡር ኩባኒያ የቀን ሰራተኞች የችግሩ መንስዔ ደግሞ ሌላ ምንም ነገር ሳይሆን ሙስና ነው ይላሉ።
CREC በመባል የሚታወቀውን የቻይና ተቁዋራጭ ኩባኒያ ለማነጋገር ያደረግነው ተደደጋጋሚ ሙከራ ኣልተሳካም። ይሁን እንጂ EREC ንም ሆነሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ኣካላት ለማነጋገር ጥረታችን ይቀጥላል።
ጃፈር አሊ
ሂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ