1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምዕራብ አገሮች በሊቢያ ላይ የሰጡት አስተያየት

ሰኞ፣ ነሐሴ 16 2003

የዛሬ ስድስት ወር ግድም የሊቢያ አማጽያን የሞአመር ጋዳፊን መንግስት ለመገርሰስ የጀመሩትን ትግላቸዉ ድል እያሳየ ነው።

https://p.dw.com/p/RhOF
ምስል picture-alliance/dpa

ትሪፑሊ ውስጥ የጋዳፊ ልጆች መያዛቸው ሲዘገብ ጋዳፊ ያሉበት ግን እስካሁን አልታወቀም። ምንም ይሁን ምን የጋዳፊ በስልጣን በቆየት በሰአታት ቢበዛ ደግሞ በቀናት ብቻ ነው የሚቆጠረው። ይህም የምዕራብ አገሮችን አስደስቷል። የዮ ኤእ አሜሪካ ፕሬዚዳን ባራክ ኦባማ «ሙአመር አል ጋዳፊና መንግስታቸው የአገዛዝ ጊዜያቸው ማብቃቱ ግልፅ ሊሆንላቸው ይገባል» ሲሉ የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጊዶ ቬስተቬለ ደግሞ፤ ለሊቢያ እና ለአለም ታሪካዊ ሰዓታት ብለውታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ