1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምዕራባዉያኑ የገና አከባበር በአዲስ አበባ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 16 2009

የጎርጎረሳዉያኑን የቀን ቀመር የሚከተሉና የፈረንጆቹን የገና በዓል የሚያከብሩ ምዕመናን በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ በመሰባሰብ ቀኑን አክበረዉ መዋላቸዉ ተሰምቶአል።

https://p.dw.com/p/2UrWq
Weihnachtsshopping Geschenke Kaufrausch
ምስል Imago

Ber. A.A (Deutsche Weihnacht spical aus Äthiopien) - MP3-Stereo

 

አብዛኞቹ ዴፕሎማቶች በተለይ በምዕራባዉያኑ ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀዉን ይህን በዓል በሃገራቸዉ ከቤተሰቦቻቸዉ በጋራ ለማክበር የረፍት ጊዜን በመዉሰድ ወደ የሃገራቸዉ መጓዝ የጀመሩት የገና በዓል ሊከበር ገና ሳምንታት ሲቀረዉ ጊዜ ጀምሮ ነዉ። እንድያም ሆኖ የምዕራቡን ዓለም ብርድ በመሸሽ ፀሐይን በመሞቅ የገናን በዓል በኢትዮጵያ ለማክበር የወሰኑ አንዳንድ አዉሮጳዉያንም አልጠፉም፤ የምዕራቡን ባህልም የያዙና ይህን የገና በዓል የሚያከብሩ ኢትዮጵያዉያንንም አግኝተናል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዩኃንስ ገብረ እግዚአብሄር እንደዘገበዉ፤ ይህንን ገና በዓል አዲስ አበባ ላይ ያከበሩት አዉሮጳዉያን ከፀሐይዋ ሙቀት በተጨማሪ ባህላዊዉን የኢትዮጵያ ቡና አስፈልተዋል፤ የእንጀራ ማዕድንም ቆርሰዋል።

ዮኃንስ ገብረግዚአብሔር

አዜብ ታደሰ