1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምስጋና ዓዉደ ርዕይ

ሐሙስ፣ መስከረም 5 2009

«እንደነዚህ ዓይነት ታሪክ ለሰሩ ሰዎች ምንም የተደረገላቸዉ ነገር የለም። እነሱ ግን ለአንድ ሰዉ ሳይሆን ለጥበቡ ባለሞያዎች ሁሉ ትልቅ የሆነ ታሪክን ነዉ ጥለዉን ያለፉት። ይህን ዉለታ ላደረጉልን ሰዎች ግን በአፀፋዉ ምንም ነገር አላደረግንላቸዉም፤ የበሚል ነበር ዝግጅቱን ያሰብነዉ»

https://p.dw.com/p/1K3HP
Äthiopien Addis Abeba Gemälde von Maler Birtukan Dejene
ምስል Birtukan Dejene

የምስጋና ዓዉደ ርዕይ


ባለፈዉ ሰምወን አንጋፋዉ ሰዓሊ ተስፋዩ ንጋቱን ለማምስገን የስዕል እግዚቢሽን ካዘጋጁት ሰዓሊያን መካከል ሰዓሊ ብርቱካን ደጀኔ ነበር ያደመጥነዉ። ጤና ይስጥልኝ አድማጮች እንደምን ሰነበታችሁ በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ የሆኑና በግልም ሆነ በተለያዩ ተቋማት ዉስጥ በሥነ-ጥበብ ሞያ ተሰማርተዉ የሚገኙ ሰዓሊዎች በመድሐንያለም መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ላይ ሳሉ በሥነ ጥበብ ሞያቸዉ መሠረት እንዲይዙና በሥነ-ጥበብ እንዲያበለጽጉ ከፍተኛ ድጋፍ ሰጥተዉናል ያሉዋቸዉ አንጋፋዉ የስዕል መምህር ተስፋዩ ንጋቱን በማመስገን የስዕል እግዚብሽን አሳይተዋል። የእለቱ ዝግጅታችን የሥነ ጥበብ ባለሞያዎችን በእንግድነት ጋብዟል።

Äthiopien Addis Abeba Gemälde von Maler Birtukan Dejene
ምስል Birtukan Dejene


ሥነ-ጥበብን በአዲስ አበባ ጉለሌ በሚገኘዉ መድሐንያለም ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዉስጥ አስተምረዉ በርካታ ባለሞያዎችን አፍርተዋል። ዛሬ ጡረተኛ ቢሆኑም ቀለምና ቡሩሽን ይዘዉ አሳሳል ማስተማርን ተሰጦ ያላቸዉን ታዳጊ ሕጻናትን በሥነ-ጥበብ መግራትን አላቋረጡም። ትናንት በስዕል ገበታ ጥበቡን ያሳይዋቸዉ ልጆች ዛሬ ተሰባስበዉ ይኸዉ ባሳዩን መሰረት እዚህ ደርሰናል ሲሉ የምስጋና ዝግጅትና የስዕል ዓዉደርዕይ አዘጋጅተዉላቸዋል። ሰዓሊ ብርቱካን ደጀኔ ለስዕል መምህር ተስፋዬ ንጋቱ የእናመሰግናለን መሰናዶን ዋና አዘጋጅ ናት። ይህን ዝግጅት ለማቅረብ የተነሳንበት አጋጣሚ ትላለች።

«ይህ አጋጣሚ ሊመጣ የቻለዉ ጋሽ አለ፤ ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ በቀብሩ ስርዓት ላይ ለነዚህ ዓይነት ታሪክ ለሰሩ ሠዎች ምንም የተደረገላቸዉ ነገር የለም። እነሱ ግን ለኛ ለአንድ ሰዉ ብቻ ሳይሆን ለጥበቡ ባለሞያዎች በሙሉ ትልቅ የሆነ ታሪክን ነዉ ጥለዉን ያለፉትና እነዚህን ሰዎች ግን አንድ ነገር አላደረግንላቸዉም፤ ማስታወሳ እንኳ አላዘጋጀንላቸዉም በሚል ነበር። ለጋሽ ዓለም የምስጋና ፕሪግራም ሳይደረግ አለፉብን።

Äthiopien Addis Abeba A-Group-of-Student-of--“Alle-School-of-Fine-Arts-and-Design”
ምስል privat

ጋሽ ተስፋዩ ንጋቱን በርካታ የጥበብ ልጆች ያፈሩ ናቸዉ፤ ትልቅ ቦታ ላይ ያሉ ልጆች ናቸዉ። እና ሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት ዉስጥ ሲገባ ተማሪዎችን የማን ተማሪ ነህ ተብሎ ቢጠየቅ አብዛኛዉ የሚለዉ ጋሽ ተስፋዬ ጋር ተምሪ የመጣሁ ነኝ ነዉ የሚለዉ። እኔ ሥነጥበብ ትምህርት ቤት በገባሁ ሰዓት 15 ተማሪዎችን ነበር የሚቀበለዉ ከነዛ 15 ተማሪዎች ዉስጥ አሸንፈዉ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ዉስጥ ሊገቡ የሚችሉት አስሩ ተማሪዎች የጋሽ ተስፋዬ ናቸዉ።

Äthiopien Addis Abeba Gemälde von Maler Birtukan Dejene
ምስል Birtukan Dejene

በእዉቀታቸዉ አልፈዉ የሚገቡ ልጆች ማለት ነዉ። እና እኝህ ሰዉ በጥበቡ በጣም ትልቅ አስተዋጽዖን አበርክተዋል ማለት ነዉ። እናም እንደዚህ አይነት ሰዎች መታወስ ይገባቸዋል ፤ ለአንድ ሰዉ ብቻ ሳይሆን ለአገርም ራሱ ትልቅ ታሪክ የሰሩ ሰዉ ናቸዉ። ስለዚህም ለምንድን ነዉ እኝህን ሰዉ የሆነ ነገር አሰባስበን እናመሰግናለን አንላቸዉም ብለን አሰብን።


በአዲስ አበባ አለ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት ተመራቂዋ ሰዓሊ ብርቱካን፤ በ1988 ዓ,ም በግራፊክስ ተመርቃለች። ትምህርትዋን እንደጨረሰችም የርዳታ ድርጅት ዉስጥ ትሰራ እንደነበር፤ ከዝያም እለታዊ አዲስ በሚል ጋዜጣ ላይ «በካርቶኒስት» ሴልማ በመባል የሚታወቀዉ የሴቶች የልማት ማኅበር ዉስጥ በፓስተር አዘጋጅነትና «ኢሉስትሪተር» ሞያ ትሰራ እንደነበር እንዲሁም በቁምነገር መጽሔት ላይ ፤ በመቀጠል አዲስ አበባ በሚገኘዉ በናዝሬት የልጃገረዶች ትምህርት ቤት በሥነ-ጥበብ መምህርነት አገልግላለች። በአሁኑ ወቅትም በግልዋ የራስዋን ተሰጥዎ ለማጎልበት በግልዋ የስዕል ስቱድዩ ዉስጥ እየሰራች እንደሆነም ገልጻለች።


ለስዕል መምህሩና ጡረተኛዉ ተስፋዬ ንጋቱ እናመሰግናለን ብለን ስጦታ መስጠት ብቻ ሳይሆን እኛ ራሳችን የት ቦታ እንደደረስን ማሳየቱ ለመምህሩና ለሞያ አባታችን ትልቅ ስጦታ ነዉ ብለን በማሰባችን የምትለዉ ሰዓሊ ብርቱካን፤ በሥነ-ስርዓቱ ላይ ያሳየናቸዉ ተማሪዎቻቸዉ በስዕል ሞያቸዉ የት እንደደረሱ እንዲያዩ ስዕሎቻቸዉን ነዉ ያሳየናቸዉ። በስዕል ያበለፀጉዋቸዉ ልጆቻቸዉ የት እንደደረሱ እንዲያዩ ዉጤታቸዉን ይዩት የመምህር ተስፋዩ ኃይል እዚህ ጋ እንዳደረሳቸዉም እንዲያዉቁት ነዉ። እንደአጋጣሚ እሳቸዉ ሲመለከቱትም ፤ በጣም ተለዉጣችኋል ሲሉ ነዉ አስተያየት የሰጡት። ጥበቡ አድጎአል ማለት ነዉ በጣም አስፍታችሁታል ሲሉም ተናግረዋል፤ በጣምም ተደስተዋል።

Äthiopien Addis Abeba Gemälde von Maler Birtukan Dejene
ምስል Birtukan Dejene


በመድኃንያለም መለስተኛ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በስዕል ትምህርት የጥበቡን መንገድ ያገኘሁት በመምህር ተስፋዬ ንጋቱ ነዉ ያለን ሰዓሊ ዲሜጥሮስ ኪዳኔ፤ በእናመሰግናለን ዝግጅቱ ላይ ከተሳተፉት የመምህር ተስፋዬ የሥነ ጥበብ ልጆች መካከል አንዱ ነዉ። ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ