1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምስራቅ ኮንጎ ውዝግብና የናይሮቢው ድርድር

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 4 2001

ዓለም አቀፍ የርዳታ ድርጅቶችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የሚያወጡዋቸው ዘገባዎች፡ በምስራቅ ኮንጎ የቀጠለው ውዝግብ በዚሁ አካባቢ የሚኖረው ህዝብ የሚገኝበትን አሳሳቢ ሁኔታ እያራዘመው ነው።

https://p.dw.com/p/GFMh
ልዩው የተመድ የኮንጎ ልዑክ ኦሉሴጉን ኦባሳንዦ
ልዩው የተመድ የኮንጎ ልዑክ ኦሉሴጉን ኦባሳንዦምስል dpa

ይህንኑ የምስራቅ ኮንጎ ውዝግብ ለማብቃት በተመድ ልዩ የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሬፑብሊክ ልዑክ ኦሉሴጉን ኦባሳን ሸምጋይነት በኬንያ መዲና ድርድር ተጀምሮዋል። ድርድሩ የተሳካ ውጤት ማስገኘቱን ግን ብዙዎች ከወዲሁ እያጠያየቁ ነው።