የምርጫ ዘመቻ በብሪታንያ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 27 2002ማስታወቂያ
ድምፅ መስጠት የሚችለዉ የብሪታንያ ህዝብ ስድስት መቶ ሀምሳ አዳዲስ እንደራሴዎችን ይመርጣል። በዚሁ ምርጫ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውድድር ቢቀርቡም፡ ዋነኞቹ ተፎካካሪዎች ጠቅላይ ሚንስትር ጎርደን ብራውን የሚመሩት ገዢው የሌበር ወይም የሰራተኛው ፓርቲ፡ የተቃውሞ ወገኖች፡ ማለትም ዴቪድ ካሜሮን የሚመሩት የኮንሰርቫቲቩ ወይም የወግ አጥባቂው እንዲሁም፡ ኒክ ክሌግ የሚመሩት የሊበራል ዴሞክራቶቹ ወይም ለዘብተኛ ዴሞክራቶቹ ፓርቲዎች ናቸው።
ድልነሳ ጌታነህ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ