የምሕረት ቅዱስ ዓመት ክብረ በዓል በቫቲካን
ማክሰኞ፣ ኅዳር 28 2008ማስታወቂያ
በከፍተኛ የፀጥታ ጥበቃ በተካሄደው በዚህ ታላቅ ክብረ በዓል ላይ ስርዓተ-ፀሎት ያደረጉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ «ፍርኃትና ሰቆቃን ወደኃላ መጣል ያስፈልገናል» ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። በኢጣልያ ዋና ከተማ በሮም የፀጥታ ጥበቃው ተጠናክሮ በአብዛኛዉ ቦታ የበረራ እገዳ ተደርጎ ነበር ፤ ማንኛዉም አይነት ነዳጅም ሆነ የጦር መሣርያን እና ተቀጣጣይ ነገሮችን የጫኑ ተሽከርካሪዎe ወደ ከተማይቱ ማዕከል እንዳይወጡ ተክልክለውም ነበር ። እዚህ ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በሮማ ኢጣልያ ወኪላችንን ተክለዝጊ ገብረየሱስን፤ ስለ ምኅረት ቀን ምንነትና ዝግጅቱ ጠይቄዉ ነበር
ተክለዝጊ ገብረየሱስ
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ