1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማጉፉሊ እርምጃ

ረቡዕ፣ ጥር 18 2008

ፕሬዝደንቱ የመንግሥት ወጪን ለመቀነስ ለበዓላት፤ ለሥብሰባና ለምርቃት የሚዘጋጁ ድግሶች፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጉዞዎች እና አበሎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲሰረዙ አዘዋል።

https://p.dw.com/p/1Hkl0
ምስል Getty Images/AFP/D. Hayduk

[No title]

አዲሱ የታንዛኒያ ፕሬዝደንት ጆን ማጉፉሊ በሙስና እና በሙስኛ ፖለቲከኞች እና ባለሥልጣናትን ላይ የከፈቱትን ዘመቻ እንደቀጠሉ።ፕሬዝደንቱ ሠሞኑን በሙስና የጠረጠሯቸዉን የሐገሪቱን ምድር ባቡር፤ የወደብ አገልግሎት፤ የኤሌክትሮኒክ መታወቂያ አዘጋጅ መስሪያ ቤት ሐላፊዎችንና ባልደረቦችን ከሥራ አግደዋል። ፕሬዝደንቱ የመንግሥት ወጪን ለመቀነስ ለበዓላት፤ ለሥብሰባና ለምርቃት የሚዘጋጁ ድግሶች፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጉዞዎች እና አበሎች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲሰረዙ አዘዋል። በዓለም አቀፉ የሙስና ደረጃ አጥኚ ተቋም በትራንስፓራንሲ ኢንተርናሽናል ጥናት መሠረት ታንዛኒያ በሙስና ከ168 ሐገራት 117ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።ሥለ ታንዛኒያዉ ፕሬዝደንት እርምጃ የናይሮቢ ተባባሪ ወኪላችን ፋሲል ግርማን በስልክ ጠይቄዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ