1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ አሳሳቢ ጊዚያዊ ሁኔታ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 2 2006

ፈረንሳይ በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ሁለት የአየር ወለድ ጦር ባልደረቦች ከተገደሉባት በኋላ በዚያ የጀመረችውን ተልዕኮ አጠናክራ እንደምትቀጥል ትናንት ይህችኑ አፍሪቃዊት ሀገር የጎበኙት የፈረንሳይ

https://p.dw.com/p/1AXXW
ምስል ISSOUF SANOGO/AFP/Getty Images

ፕሬዚደንት ፍራንስዋ ኦሎንድ አስታወቁ። የፈረንሳይ ወታደሮች በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የተሰማሩት በሀገሪቱ በቀጠለው ውዝግብ ትጥቅ ያልፈቱ የሴሌካ ዓማፅያን በመዲናይቱ ባንግዊ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ 400 ሰዎች ከገደሉ በኋላ ነው። ፈረንሳይ እና የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮች ቢገቡም ግድያው እንደቀጠለ ነው።

የተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክን ዓለም አቀፍ የጦር ተልዕኮን ካፀደቀ ከጥቂት ቀናት ወዲህ ፈረንሳይ በርካታ መቶ ወታደሮች ውዝግብ ወዳዳቀቃት ሀገር ልካለች። የአፍሪቃ ህብረት ደግሞ በዚያ ያሰፈረውን 2500 ውደ 6000 ከፍ ለማድረግ ዕቅድ አለው። የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማም የፈረንሳይ እና የአፍሪቃ ህብረት ጦርን ለመርዳት 60 ሚልዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

የፈረንሳይ ጦር በወቅቱ በባንግዊ የሴሌካ ዓማፅያንን የጦር መሳሪያ ትጥቅ ለማስፈታቱ ተግባር ቅድሚያ ሰጥቶ መንቀሳቀስ የጀመረ ሲሆን፣ በዚሁ ወቅት ከዓማፅያኑ ጋ ብርቱ ውጊያ ባካሄደበት ጊዜ ሁለቱ ወታደሮቹ እንደተገደሉ ተሰምቶዋል። ዓማፅያኑን ትጥቅ የማስፈታቱ ተግባር ቀላል ይሆናል ተብሎ እንዳልተገመተ ለዓለም አቀፍ ውዝግቦች የመፍትሔ ሀሳብ የሚያቀርበው «ኢንተርናሽና ልክራይስስ ግሩፕ» የተባለው ቡድን ተንታኝ ቲየሪ ቪርኩሎ) ገልጸዋል።

Hollande besucht Zentralafrikanische Republik 10.12.2013
ምስል picture-alliance/AP

« የጦር መሳሪያ ትጥቅ በመፍታቱ አንፃር ብርቱ ተቃውሞ እንደሚኖር የተጠበቀ ነበር። ዓማፅያኑ የጦር መሳሪያቸውን ለመፍታት ዝግጁ አልነበሩም። »

ፕሬዚደንት ሚሼል ጆቶጂያ የሚመሩት የማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ የሽግግር መንግሥት ዓማፅያኑ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ እና በብሔራዊው ጦር ውስጥ እንዲዋኃዱ ለማግባባት ባለፈው ሰኞ ያደረገው ሙከራ ሳይሳካ ነው የቀረው። የቀድሞ የሴሌካ ዓማፅያን መቆጣጠር ያልቻሉት ፕሬዚደንቱ በሲቭሉ ሕዝብ አንፃር በየቀኑ የቀጠለውን አስከፊ ጥቃት ማስቆም ባለመቻላቸው አሁን ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ በጦር ጣልቃ የገባበትን ድርጊት በደስታ በመቀበል ሀገሪቱን እንዲያረጋጉ ተስፋ ማድረጋቸውን በፓሪስ የሚገኝ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ምርምር ተቋም ባልደረባ ዣን ክሎድ አላር ቢገልጹም፣ ሀገሪቱን ማረጋጋቱ አዳጋች እንደሚሆን ነው ያመለከቱት።

« በጣም ደካማ ሁኔታ ላይ ከሚገኘው የማዕከላይ አፍሪቃ የፀጥታ ኃይል እና ከብሔራዊው ጦር ጋ ሀቀኛ ትብብር ማድረግ አይቻልም። ምክንያቱም እንደሌሉ ነው የሚቆጠሩትና። በነዚህ ኃይላት ውስጥ ከሚጠቃለሉት መካከል አንዳንድዶቹ ከሴሌካ ዓማፅያን ጋ ተባብረው ይሰራሉና። »

ይሁንና፣ የፈረንሳይና የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮች አሁን በማዕከላይ አፍሪቃ ሬፓብሊክ ውስጥ መሰማራት ብቻ ሀገሪቱን ማረጋጋት መቻላቸውን የሂውማን ራይትስ ዎች የአፍሪቃ ጉዳዮች ተንታኝ ልዊስ ማጅ ይጠራጠሩታል።

በጥቂት ሺህ የሚቆጠሩ የፈረንሳይ እና የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮች መሰማራታቸው ጥሩ ጅምር ቢሆንም በቂ አይደለም። ዘላቂ ሰላም እንዲወርድ እና የሰብዓዊ ርዳታ ማቅረብ እንዲቻል እና ለውዝግቡም ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲገኝ ከተፈለገ ተጨማሪ ወታደሮች በሀገሪቱ መሰማራት ይኖርባቸዋል።»

ከዚህ በተጨማሪ ግን የሴሌካ ዓማፅያን የባንግዊ መንግሥት በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ከፊል የሚገኙት በብዛት የሙሥሊም እምነት ተከታዮ የሆኑ ዜጎችን እና ያካባቢውn ልማት ችላ ብሎዋል በሚል ለዓመፅ ያበቃቸውን ሁኔታ ማስተካከሉ ለውዝግቡ ማብቃት ዋነኛ ሚና እንደሚጫወት ተንታኞች ጠቁመዋል።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ