1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማክስ ፕላንክ ተቋም 100ኛ ዓመት፣

ሐሙስ፣ ጥር 5 2003

በጀርመን ሀገር አያሌ ተመራማሪዎችን ያቀፈውና በአገሪቱ በመላ አያሌ ቅርንጫፎች ያሉት የማክስ ፕላንክ የምርምር ተቋም፤ መቶኛ ዓመቱን ደፈነ።

https://p.dw.com/p/QrcD
አ ጎ አ በ 1918 በፊዚክስ የኖቤል ሽልማት ያገኙት፤ ማክስ ፕላንክምስል Max-Planck-Gesellschaft

ተቋሙ፣ ትናንት፣ በርሊን ውስጥ፣ በኪነ ጥበብ አካዳሚ አዳራሽ ፤ የተቋቋመበትን 100ኛ ዓመት አክብሯል። በዚሁ ክብረ በዓል ላይ የተገኙት ዋናው የክብር እንግዳ፣ አሁን የ92 ዓመት ጎምቱ የሆኑት ፣የቀድሞው የጀርመን መራኄ መንግሥት ፣ ሔልሙት ሽሚት ናቸው። ሽሚት በክብረ በዓሉ ላይ ባሰሙት ንግግር፣

«በአሁኑ ጊዜ፣ በዓለም ህዝብ ላይ የተደቀኑ ዐበይት ችግሮች፣ የህዝብ ቁጥር አለቅጥ መናር፤ መጠን የለሽ የጦር ሣሪያ ትጥቅ፣ የምድራችን ግለት እየጨመረ መምጣትና ዓለም አቀፉ ፣ አጽናፋዊው የኤኮኖሚ ትሥሥር ናቸው» ብለዋል።

ጤናይስጥልኝ እንደምን ሰነበታችሁ? በዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራችን ፣ የማክስ ፕላንክን ተቋም የ100 ዓመታት የምርምር ታሪክ በአጭሩ እንቃኛለን።

(ድምፅ)------

ተክሌ የኋላ