1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማላዊ ሴቶች የፓርላማ ተሳትፎ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 4 1998

በማላዊ የአገር አስተዳደር ስልጣን ደረጃዎች ላይ ሴቶች መሳተፍ የጀመሩት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ቢሆንም እየታየ ያለዉ እርምጃ የፆታ እኩልነት መርሆዎችን የሚደግፍ ሆኗል። በተለይ ባለፈዉ ዓመት ሂደቱ ፈታኝ ቢሆንባቸዉም በርከት ያሉ ሴቶች የአገሪቱን የፓርላማ መቀመጫዎች ለማግኘት ችለዋል። እርምጃዉ ባጠቃላይ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት አገራት በጋራ ሊፈፅሙት ያቀዱት ቢሆንም እንደታሰበዉ ግን አብዛኛዎቹ አልተሳካላቸዉም። ሶስት ሀገራት ደግሞ ምሳሌ የሚሆን

https://p.dw.com/p/E0jG

��ረት እያደረጉ ነዉ።

ከአንድ ዓመት በፊት በርካታ ሴት ማላዉያን በወንዶች ተፅዕኖ ስር የነበረዉን የአገራቸዉን የአስተዳደር ስርዓት አሸንፈዉ በህግ ማርቀቅና ማፅደቅ ተግባር ለመሳተፍ ፓርላማ ገቡ።
ምንም እምኳን በፓርላማዉ በርካታ ወንበር ማግኘታቸዉ አንድ እርምጃ ቢሆንም በየግል ህይወታቸዉ ከተጫነባቸዉ ኃላፊነት ጋር የገቡበት የአገር ኃላፊነት ፈታኝ መሆኑን ይናገራሉ።
ከእነሱ መካከል ልጅ የልጅ ልጅ እንዲሁም የእህትና የወንድም ልጆች አብዛኛዎቹ ወላጆቻቸዉን በሞት የተነጠቁ ተንከባካቢ የሆኑት ባላቸዉን በሞት ያጡት የ50ዓመቷ ወይዘሮ ጌርትሩድ ሜካንዳዊሬ ይገኛሉ።
በአጭር ጊዜ ቆይታ እንዳዩት እንክብካቤ የሚፈልጉ የበርካታ ህፃናት እናት ሆኖ የፓርላማ አባል መሆን ከባድ ሆኖባቸዋል።
እዉነቱን ለመናገር እነዚህን ህፃናት በኃላፊነት ይዤ በፓርላማ ሃገራዊ ጉዳይ ለመፍታት መግባቴ አስቸግሮኛል ምክንያቱም በዚህ ከባድ ሃላፊነት መካከል ከሁለቱ አንዱ ወገን የግድ ችግር ይገጥመዋል ይላሉ።
በፆታ ሳቢያ ተፅዕኖ በመኖሩም ወደፓርላማዉ ለመግባት ያደረጉት ጥረት በቀላል የሚታይ አልነበረም።
በሚኖሩበት አካባቢ በሰሜናዊ ምዚምባ ሶሎራ ቀበሌ የሚገኙትን የኖጎኒ ወግ አጥባቂ ወገኖች የሴትን በፓርላማ መሳተፍ አስፈላጊነት ለማሳመን ያደረጉት ሙከራ ብዙ አልፍቷቸዋል።
አሁን ግን እነዚሁ ወንዶች የማካንዳዊሬን በአስተዳደር ደረጃ ለመሳተፍ በመካከላቸዉ መገኘትን ስለተቀበሉት ሰላም አግኝተዋል።
እንደዉም ይላሉ ማካንዳዊሬ እስከዛሬ ወንዶችን ብቻ በፓርላማ በመምረጥ ለአገራቸዉ የልማት አጋጣሚዎችን በከንቱ በማሳለፋቸዉ ተፀፅተዋል።
ያሁሉ ትችትና ቅሬታ ተለዉጦም ዛሬ የተገላቢጦሽ ልክ እንደእናት እየተንከባከቧቸዉ እንደሚገኙ የተቃዋሚዉ ፓርቲ አባል የሆኑት ማካንዳዊሬ ይናገራሉ።
ሌላዋ የወግና ባህል ማነቆዉን ጥሰዉ በግል በመወዳደር የማላዊ የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሚኒስትር ለመሆን የበቁት ማርጆሪ ናጉንጂ ናቸዉ።
የእሳቸዉን የስልጣን ደረጃ ግን አንዳንዶች ፕሬዝደንት ቢንጉ ዋ ሙታሪካ አዲስ ያቋቋሙት የዲሞክራቲክ እድገት ፓርቲ በምህፃሩ ዲፒፒ አባል ለማድረግ አስበዉ ነዉ በሚል ይተቹታል።
ሙታሪካ እንደሚሉት በአስተዳደራቸዉ ሙስናን ለመዋጋት በሚል የጀመሩት እርምጃ ከዩዲኤፍ አባላት ወገን ችግር ቀስቅሷል።
ሌሎች የፓርማላ አባላትንም ወደዲፒፒ ለመሳብ በሚያደርጉት ጥረት የዩዲኤፍ አባላት ሙታሪካን የተለያየ ክስ ይሰነዝሩባቸዉ ጀምረዋል ከክሶቹ መካከልም ዲፒፒን ለማቋቋም ሲሉ የመንግስት ገንዘብ አባክነዋል ዋነኛዉ ነዉ።
የማንም ፓርቲ አባል አይደለሁም ከመንግስት ጋርም ለመስራት የምመርጠዉ በዚህ መልክ ነዉ በማለትም ናጉንጂ በበኩላቸዉ የሚሰነዘረዉን ትችትና ጥርጣሬ አጣጥለዉታል።
እሳቸዉ እንደገለፁት በአገሪቱ ካቢኔ ያላቸዉ ቦታ የብሄራዊ ሃላፊነትን የሚወጡበት እንደመሆኑ መጠን ለተራ ተግባራት ማስፈፀሚያ ይጠቀሙበታል ብሎ ማሰብ ስህተት ነዉ።
ከአገሪቱ የፖለቲካ ምሁራን መካከል ሴቶች በፓርላማ መሳተፋቸዉ መልካም ሆኖ ሳለ የማላዊን ችግር ለመፍታት ለሚደረገዉ ሙከራ አዲስ የሚባል ዘዴ ሲያቅረቡ አልታዩም በማለት ይተቻሉ።
በዚያዉ መጠን ደግሞ በዚህ በአንድ ዓመት ዉስጥ ብዙ ለዉጥ ባንጠብቅም ቁጥራቸዉ በፓርላዉ ጨምሮ መታየቱ አንድ ለዉጥ ነዉ ይላሉ የማላዊ ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካ ሳይንስ ዘርፍ የበላይ የሆኑት ቦኒፌስ ዱላኒ።
በአሁኑ ወቅት ከ193 የፓርላማ አባላቱ መካከል 27ቱ ሴቶች ናቸዉ ይህም ማለት ከአጠቃላዩ ቁጥር 14 በመቶ ይሆናል።
በደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ በምህፃሩ SADC ካለፈዉ የፈረንጆቹ 1997 እስከ 2005 ድረስ የሴቶችን በመንግስት የዉሳኔ ሰጪነት ስልጣን ተሳትፎ 30በመቶ ለማድረስ ታቅዶ ነበር።
ምንም እንኳን ከ14ቱ የSADC አባል ሀገራት መካከል 11ዱ የታለመዉን ግብ መምታት ባይችሉም አሃዙ ካለፈዉ ነሃሴ ወር ጀርሞ ወደ50 በመቶ ከፍ ብሏል።
ደቡብ አፍሪካ፤ ማዉሪታንያና ሞዛምቢክ በአገር አስተዳደር የዉሳኔ ሰጪነት ሶስት የስልጣን ደረጃዎችን ለሴቶች በመልቀቅ ተሳክቶላቸዋል።
በፓርላማዉ ከታየዉ ከእንዲህ አይነቱ ዉዝግብ ባሻገር በሌላ ዉገን ያለዉ ህይወት ካጋጠመዉ የምግብ እጥረት ሌላ ችግር እምብዛም አልነበረዉም።
አገሪቱ የምትገኝበትን የችግር ደረጃ የሚመረምረዉ ኮሚቴ በያዝነዉ ወር እንዳስታወቀዉ ከ4ሚሊዮን በላይ ማለትም የማላዊ ህዝብ ቁጥር ግማሽ የሚሆነዉ ወገን የእርዳታ ምግብ አቅርቦት ጠባቂ ነበር።