የማሊ ወቅታዊ ሁኔታ5 ነሐሴ 2007ማክሰኞ፣ ነሐሴ 5 2007በማሊ የሽብር ጥቃት በተደጋጋሚ እየተከሰተ መሆኑ ተነገረ። የሀገሪቱ መንግሥት እንዳስታወቀው ከሆነ ለጥበቃ የተሰማራ ወታደራዊ ተሽከርካሪ ፈንጂ ረግጦ በመንጎዱ ቢያንስ ሦስት ወታደሮች ተገድለዋል። ጥቃቱ የደረሰው 4የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኖችን ጨምሮ 13 ሰዎች ሆቴል ውስጥ በተከሰተው የአጋች ታጋች ግብግብ ከተገደሉ ከ4 ቀናት በኋላ መኾኑ ነው።https://p.dw.com/p/1GDZuምስል Getty Images/AFPማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለእረፍት ተዘግቶ አብዛኞቹ አባላቱ ወደየመኖሪያ ቀዬያቸው አቅንተዋል። ከሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል ለመጡ አብዛኞቹ የምክር ቤት አባላት ግን በአሁኑ ወቅት ወደ መጡበት መመለስ የሚታሰብ አይደለም። ግድያ እና የፈንጂ ጥቃት በማሊ ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። ፊሊፕ ዛንድነር/ይልማ ኃይለ ሚካኤል ማንተጋፍቶት ስለሺ አርያም ተክሌ