1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የማሊ ቀዉስ እና የተኩስ አቁም ንግግር

ሰኞ፣ ሰኔ 3 2005

የማሊ መንግሥትና፤ በአገሪቱ የሚገኙት የቱዋሪግ ዓማጺያን የተኩስ አቁም ድርድር ጀመሩ። ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ የጀመረዉ ይህ ንግግር፤ በአገሪቱ በሚቀጥለዉ ወር ከሚካሄደዉ ብሄራዊ ምርጫ በፊት በሰሜናዊ ማሊ የሚታየዉን ዉዝግብ ለመፍታት እንደሆነ ታዉቋል።

https://p.dw.com/p/18nFL
A soldier from the Tuareg rebel group MNLA holds an AK-47 in the northeastern town of Kidal February 4, 2013. Pro-autonomy Tuareg MNLA fighters, whose revolt last year defeated Mali's army and seized the north before being hijacked by Islamist radicals, have said they are controlling Kidal and other northeast towns abandoned by the fleeing Islamist rebels. Picture taken February 4, 2013. REUTERS/Cheick Diouara (MALI - Tags: POLITICS CIVIL UNREST CONFLICT) // eingestellt von se
ምስል Reuters

ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት «አምንስቲ ኢንተርናሽናል» ባለፈዉ ሳምንት የማሊ መንግስት ጦር እና የሰሜናዊ ማሊ ዓማጺያን ሰላማዊ ሰዎችን መግረፍ መግደልና ደብዛቸዉን ማጥፋታቱን ማጋለጡ የሚታወስ ነዉ።

FILE - Malian families arriving in the Bamako bus station waiting to receive their possessions after a long journey from Timbuktu, northern Mali, on 11 April 2012. The MNLA, a Tuareg seperatist rebel group, and Ansar Dine, another rebel group wishing to impose Sharia Law upon Mali, have both claimed occupation of Timbuktu and other cities in Northern Mali, prompting many to flea the region. EPA/Tanya Bindra (Zu dpa KORR "Afrika vor turbulentem 2013: Kampfzonen im Sahel und Zentralafrika") pixel
ምስል picture-alliance/dpa

የማሊ መንግስት እና MNLA በሚል አሕጽሮት የሚጠራው የአገሪቱ ቱዋሬግ ቡድን ዓማጺያን፤ በጎረቤት ሀገር ቡርኪና ፋሶ ነዉ ባለፈዉ ቅዳሜ የተኩስ አቁም ንግግር የጀመሩት። በቡርኪናፋሶ ሸምጋይነት የተጀመረዉ የዚህ ድርድር ዋና አላማ በማሊ ለሚታየዉ ከባድ ቀዉስ ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት መሆኑን የቡርኪናፋሶ ፕሪዚደንት ብሌዝ ኮምፓዎሪ ተናግረዋል። ፕሪዚደንት ኮምፓዎሪ የተረጋገጠ ደህንነት ለማስገኘት፤ ነጻ እና ፍትሃዊ ምርጫ ለማካሄድ የማሊ መንግስት ወታደሮች እና ዓማጺያን በመካከላቸዉ የሚያካሂዱትን ዉግያ እንዲገቱ ጠይቀዋል። በቱዋሪግ ዓማጽያን በተያዘችዉ ኪዳል ከተማ አካባቢ ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ የተጀመረዉ ከፍተኛ ዉግያ፤ ከአንድ ወር ግድም በኋላ ሐምሌ 28 በማሊ ሊደረግ የታቀደዉን የፕሪዚደንታዊ ምርጫ አጠያያቂ አድርጎታል። MNLA የአገሪቱ ቱዋሬግ ዓማጺያን ቡድን ምክትል ፕሪዚደንት ማሃማዱ ጄሪ ማይጋ፤ ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ከማሊ መንግስት ጋር ስለተጀመረዉ ንግግር ለዶቼ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ፤ «በዚህ ዉይይት ላይ ሁለታችንም በጣም ጥሩ ነገርን ፈልገን ነዉ የቀረብነዉ። ከሁለታችንም ወገን ጥሩ ነገርን ለመፈጸም አንድ ነጥብ ላይ ደርስን፤ ለስምምነት የምንበቃ ይመስለናል። ዛሪ እዚህ የምገኘዉ ለሰላም ስምምነት ስለሆነ፤ በኪዳል ከተማ አካባቢ ስለነበረዉ ጦርነት ምንም መናገር አልፈልግም፤ ምክንያቱም ያ ያለፈ ነገር ነዉ። በእኛ አስተሳሰብ አንድ ጦርነት ወይም ትግል ካለፈ ፤ ስለዛ ጦርነት የሚያስብ የለም ይረሳል።»

ባለፈዉ ጥር ወር በአማጽያን የተያዘችዉን ከተማ ኪዳል ለማስለቀቅ በፈረንሳይ ጦር የሚታገዘዉ የማሊ መንግሥት ጦር እና (MNLA)አማጺያን ቡድን በገጠሙት ዉጊያ ወደ 30 የሚጠጉ አማጽያን እና ሁለት የመንግስት ወታደሮች ተገለዋል። የማሊ መንግሥት በመጪዉ ሐምሌ ምርጫ ከመደረጉ በፊት፤ ከተማይቱን ከአማጺያን ለማስለቀቅ በተደጋጋሚ ቢሞክርም አልተሳካለትም። በርካታ የማሊ መንግስት ተጠሪዎች አማጺያኑ ኪዳልን እንደተቆጣጠሩ ምርጫ የሚደረግ ከሆነ ትክክለኛ ምርጫ ሊሆን አይችልም ሲሉ በመናገር ላይ ናቸዉ። ባለፈዉ ቅዳሜ በቡርኪና ፋሶ በማሊ መንግስት እና በቱዋሪግ አማጺያን መካከል በጀመረዉ የመፍትሄ ንግግር ላይ የሰሜናዊ ማሊ መልክተኛ፤ ቴቢሌ ድራሜ እንደሚሉት

©Xavier Malafosse/Wostok Press/Maxppp France, Montpellier 31/05/ 2008 Moussa Ag Assarid, porte parole du MNLA (Mouvement national pour la libération de l'Azawad),qui vient de proclamer l'independance de l'Alawad au Nord Mali assiste a lla Comedie du Livre a Montpellier Schlagworte Politik, Personen, Konflikte, Rebellen, Tuareg, Widerstand, Kopfbedeckung
ምስል picture-alliance/dpa

«የማሊ መንግስት ለፕሪዚደንታዊ ምርጫ እጅግ ጥሩ እና የተመቻቸ ሁኔታን ለመፍጠር ፤ በሚቀጥሉት ቀናት በሰሜናዊ ማሊ ከሚገኙት ታጣቂ አማጺያን ጋር አንድ ስምምነት ላይ መድረስን ይፈልጋል። የማሊ ህዝብ የሚመርጠዉ ፕሪዚደንትአገሪቱን ለረጅም ግዜ ሲደቁስ የኖረዉን ዉጥረት ከታጣቂ አማጽኑ ጋር ዉይይት በማድረግ መፍትሄ ላይ እንዲደርስ ይጠበቅበታል። እነዚህ ዉይይቶች ደግሞ ከማንኛዉም በሰሜናዊ ማሊ ከሚገኙ ታጣቂ ቡድኖች ጋር እንዲሆን ነዉ ምኞታችን» የቀድሞዋ የቅኝ ገዥ አገር ፈረንሳይ ባለፈው ጥር ወር ወታደራዊ ዘመቻ በመክፈት፣ በማሊ እስላማዊ ዓማጺያን ቁጥጥር ስር ውሎ የነበረውን ሁለት-ሶሥተኛ የአገሪቱን ሰሜናዊ ክፍል ስታስለቅቅ ቱዋሬጎችም በአክራሪዉ አንሳር ዲን ተይዛ የነበረችዉን ኪዳልን መልሰው ይዘዋል። የፈረንሣይ ጦር ተልዕኮውን በሚቀጥለው ወር ለተባበሩት መንግሥታት ሰላም አስከባሪ ሃይል፤ እንደሚያስረክብ ይጠበቃል። ማሊ ውስጥ በመፈንቀለ-መንግሥት ከተካሄደ በኋላ የተቋቋመዉ የሽግግር መንግስት፤ በመጭዉ ሐምሌ ወር በሃገሪቱ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንደታሰበዉ ለማካሄድ፤ ከፍተኛ ጥረት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ