«የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት»የአንድነት መግለጫ
ሐሙስ፣ ሰኔ 13 2005ማስታወቂያ
አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ህዝባዊ ንቅናቄ ለመጀመር የያዘውን እቅድ ይፋ አደረገ ። ፓርቲው ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጠው መግለጫ ሰብአዊ መብቶች በህዝባዊ ንቅናቄ እንዲረጋገጡ የህብረተሰቡም ልዩ ልዩ ጥያቄዎች መፍትሄ እንዲፈለግላቸው የሚሊዮኖችን ድምፅ በማሰባሰብና በአዲስ አበባና በክልሎች ሰለማዊ ሰልፎችን በማካሄድ ጥያቄውን እንደሚያቀርብ አስታውቋል ። የህዝብ ድምፅ በማሰባሰብ የፀረ ሽብር ህግ እንዲሰረዝ ጉዳዩን ለክስ እንደሚያቀርበውም ተናግሯል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ