የሙጋቤ ሥልጣን ፍጻሜ ተቃርቦ ይሆን?
ዝምባባዌ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠች፤ ፈላጭ ቆራቹ ሮበርት ሙጋቤ በቀጣይ ጊዜያትም በሥልጣን ላይ ለመቆየት ከረጅም ጊዜ ተቀናቃኝአቸው ኖርማን ቻንጊራይ ጋር ይፎካከራሉ። ሀገሪቱ በአሁኑ ጊዜ ብርቱ የኤኮኖሚ ቀውስ እንዳጋጠማት ናት።
ዝምባባዌ አዲስ ፕሬዚዳንት መረጠች፤ ፈላጭ ቆራቹ ሮበርት ሙጋቤ በቀጣይ ጊዜያትም በሥልጣን ላይ ለመቆየት ከረጅም ጊዜ ተቀናቃኝአቸው ኖርማን ቻንጊራይ ጋር ይፎካከራሉ። ሀገሪቱ በአሁኑ ጊዜ ብርቱ የኤኮኖሚ ቀውስ እንዳጋጠማት ናት።
የአፍሪቃ የበቆሎ ጎተራ የነበረች አገር አሁን ተሟጦባታል፤
እ ጎ አ በ 1980 ነበረ ፣ ዝምባብዌ ከባሪታንያ ቅኝ አገዛዝ ተላቃ ነጻነቷን ያወጀች።ያኔ የግብርናው ኤኮኖሚ በማበብ ላይ ነበረ። ደቡባዊ አፍሪቃዊቷ ሀገርም «የአፍሪቃ የበቆሎ ጎተራ» የሚል ተቀጥላ ሥም አትርፋ ነበር። በ 1980ኛዎቹ ዓመታት ኢትዮጵያ በድርቅ ስትጠቃ፣ ከአካባቢው አገሮች፤ ምግብ ማቅረብ የቻላች ሀገር፤ ዝምባብዌ ነበረች። ይሁንና እ ጎ አ በ በ 2000 ዓ ም፤ አከራካሪ ነበረ የተባለው የመሬት አያያዝ ተሃድሶ ለውጥ ተጀመረ።
የረሃብ ቀውስ ከመሬት ይዞታ የተሃድሶ ለውጥ በኋላ፤
የሮበርት ሙጋቤ መንግሥት፣ ለንደን ውስጥ በላንካስተር አዳራሽ በተፈረመው ውል መሠረት ፤ ለም የእርሻ መሬት ለሌላቸው ጥቁሮች አርሶ አደሮች ለማከፋፈል እርምጃ ሲወስዱ ፤ የነጮች አርሶ አደሮችን ይዞታ ቀምተው እንደሰጡ ነበረ የተቆጠረባቸው። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ ውዝግብ ሳቢያ የግብርናው ዘርፍ ተጎዳ፤ ረሃብም ተከሠተ። የሙጋቤ ZANU-PF ፓርቲ ለረሃቡ ፣ ሰበብ፤ ድርቅና የምዓራቡ ዓለም የአገዳ እርምጃ መሆናቸውን ነበረ የገለጠው።
ማዕቀብ በሙጋቤ መንግስት ላይ
እ ጎ አ በ 2002 ዓ ም፤ የአውሮፓው ኅብረት በፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤና ተጓዳኞቻቸው ላይ (ለጭር ጊዜ ላልቶ የነበረውን ) ማዕቀብ ተግባራዊ አደረገ። በዚህ እርምጃ የአውሮፓው ኅብረት በዝምባብዌ ይጣሳል ላለው ሰብአዊ መብት ምላሹን ነበረ የሰጠው። ዩናይትድ እስቴትስና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF)፣ የፋይናንስ እርዳታቸውን አቆሙ።
ኤኮኖሚው ከጊዜ ወደጊዜ እያገገመ መምጣቱ፣
ከባድ የፖለቲካ ችግር ቢያጋጥማትም ፤ ዝምባብዌ ኤኮኖሚዋን እ ጎ አ ከ 2008 አንስቶ በማሳደግ ላይ ነው የምትገኘው። በዓመቱም እጅግ በገዘፈ የዋጋ ግሽበት ፍጹም ኃይል ያጣውን የዝምብባዌ ዶላር ጥቅም ላይ ማዋል ትታ፤ በምትኩ፣ በአሜሪካ ዶላር፤ በቦትስዋና ፑላ፤ በደቡብ አፍሪቃ ራንድና በብሪታንያ ፓውንድ መገልገል ያዘች። ከዚያን ጊዜ አንስቶ፤ ዓመታዊው የዋጋ ግሽበት ከ 5% በታች ሊወርድ ችሏል።
ኀይል የተንጸባረቀበት ሁከት፣
ሙጋቤ ባለፉት ዐሠርተ ዓመታት፣ ከ ZANU-PF ፓርቲያቸው ጋር፣ አገሪቱን ብቻቸውን ገዝተዋል፤ እስከ 2008 ዓም ምርጫ ድረስ። በመጀመሪያው የምርጫ ዙር ከተፎካካሪአቸው ሞርጋን ቻንጊራይ ያነሰ ድምፅ ነበረ ያገኙት። ደጋፊዎቻቸውም የቻንጊራይን ደጋፊዎች፤ ያጠቁ ነበር። በሁለተኛው ዙር ተስፋ እንደማይኖራቸው የተገነዘቡት ቻንጊራይ አፈገፈጉ ፤ ሙጋቤ እንደገና ፕሬዚዳንት ሆኑ።
የሥልጣን ክፍፍል፤
በዓለም አቀፍ ግፊት ሳቢያ፤ ሙጋቤ ሥልጣናቸውን ማካፈል ነበረባቸው። በመሆኑን ቻንግራይን እ ጎ አ በ 2008 ጠ/ሚንስትር እንዲሆኑ አደረጉ። ሙጋቤ ፤ በተሃድሶ ለውጥ የፕረስ ነጻነትን ለማክበር ፣ ጦር ሠራዊቱ፣ ከፖለቲካ ገለልተኛ እንዲሆን የገቡትን ቃል አልፈጸሙም። ያልሠመረው ጥምር መንግሥት በሐምሌ 24 ፤ 2005 ቱ ምርጫ ሳያከትምለት አይቀርም።
አዲስ ህገ-መንግሥት፣
ባለፈው ግንቦት የዝምባብዌ ተወላጆች አዲስ ህገ-መንግሥት እንዲቀርብ ድምፅ ሰጥተዋል። አዲስ የለውጥ ፈር ግን አልተቀደደም ነው የሚባለው። የ 89 ዓመቱ አዛውንት በቀጣይ 2 የምርጫ ጊዜያት ለመሳተፍ እቅድ አላቸው። አሁንም የፖሊስና የጦር ሠራዊት መሪዎችን የሚሾሙት፣ ፕሬዚዳንቱ ናቸው። ሙት በቃ ብይን አልተሻረም፤ ግብረ ሰዶማዊነት በህግ የተከ ለከለ ነው።
ከድህነት መውጣት አለመቻሉ
ዝምባብዌ፣ ፕላቲኒም፤ ድንጋይ ከሰል፤ ብረት፣ ወርቅና አልማዝ ማዕድናት ያሏት ሀገር ናት። ያም ሆኖ የአብዛኛው ህዝቧ የቀን የነፍስ ወከፍ ገቢ 1,25 የአሜሪካ ዶላር ነው80 ከመቶ ዝምባብዌአውያን፤ ኑሮአቸው ፤ ከድህነት ጠርዝ በታች ነው ። ሥራ አጡ 90% ነው።
ቤዛ ይሆናል የተባለው የአልማዝ ማዕድን
የ«ማራንጅ ማዕድን እ ጎ አ በ 2006 ነው የተጀመረው፤ በዓለም ውስጥ እጅግ ብዛት ያለው አልማዝ የተከማቸበት ቦታ ነው። ግን በዚህ የተፈጥሮ ሀብት አትራፊዎቹ ጥቂት ልሂቃን ናቸው። Partnership Africa Canada የተሰኘው ድርጅት፣ እንዳለው፣ እስካሁን ፤ 1,5 ቢሊዮን ዩውሮ ከመንግሥት ባለሥልጣንት ኪስ ነው የገባው።
የፖለቲካ ጭቆና
ያልተስተካከለ ማኅበራዊ ኑሮ ሥርዓት፤ የሰብአዊ መብት ጥሰት፤ በዝምባብዌ ዘወትር የሚታይ ነው ። እ ጎ አ በ 211፣ 46 የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ነበሩ የተያዙት። በግብፅ የለውጥ ተነሳሾችን ቪዲዮ ይዛችኋልና ፤ በዝምምባዌ ተመሳሳይ እንቅሥቃሤ ለማካሄድ አስባችኋላ ተብለው ነበረ የተያዙት።