የሙከራ ኤሌክትሪክ ሽያጭ ለጅቡቲ
ረቡዕ፣ ሰኔ 8 2003ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ኮርፖሬሽን የህዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ አዲስ ታገለ ዛሬ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ካለፈው ወር አንስቶ የሙከራው የኤሌክትሪክ ሽያጭ ተጀምራል ። ኮርፖሬሽኑ አሁን ለጅቡቲ የሚልከው ኃይል ሃያ ሜጋዋት መሆኑን አቶ አዲስ አስታውቀዋል ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እያደገ የመጣውን የሐገሪቱን ፍጆታ ማርካት አልቻለም ። በተደጋጋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ያጋጥማል ። ባላፈው ሠኞ የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሂለሪ ክሊንተን በአፍሪቃ ህብረት አዳራሽ ንግግር ሲያደርጉ እንኳን አዲስ አበባ ውስጥ መብራት ተቋርጦ ነበር ። በዚህ መሐል ነው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ውጭ መላክ የጀመረው ።
ታደሰ እንግዳው
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ