የሙባረክ መፈታትና የአረቡ ዓለም አስተያየት
ዓርብ፣ ነሐሴ 17 2005ማስታወቂያ
የ85 ዓመቱ የቀድሞው የግብፅ ፕሬዝዳንት ሆስኒ ሙባረክ ከእስር መፈታት በሃገር ውስጥ ተቃውሞም ድጋፍም አስከትሏል ። በምርጫ ሥልጣን የያዙት መሀመድ ሙርሲ በጦር ኃይሉ ከሥልጣን ተነስተው በታሰሩ በ7 ሳምንታቸው ሙባረክ ከእስር ቤት መውጣታቸው በሙባረክ ተቃዋሚዎች ዘንድ የግብፅ ህዝባዊ ንቅናቄ የመቀልበሱ ምልክት ተደርጎ ተወስዷል ። ተቃዋሚዎችን ያስቆጣው የሙባረክ መፈታት ሃገሪቱን በማረጋጋት የሚያወድሷቸውን ደጋፊዎቻቸውን ደግሞ አስደስቷል ። የሙባረክን መፈታት የአረቡ ዓለም ህዝብ እንዴት እንደተቀበለው የጂዳውን ወኪላችንን ነብዩ ሲራክ በስልክ አነጋግሪዋለሁ ።
ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ