የሙሥሊም መሪዎች የፍርድ ቤት ውሎ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 23 2006ማስታወቂያ
ቃሊቲ የወጣቶች መዝናኛ ማዕከል ዛሬ ያስቻለው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ምድብ ችሎት በሙስሊም መሪዎች ተከሳሾች ጠበቆች የቀረበውንንና አቃቤ ህግ መቃወሚያ ያቀረበበትየመከላከያ ምስክሮች ጭብጥ ላይ ብይን ሰጠ ። ችሎቱ በተከሳሽ በእነ አቶ አቡበከር አህመድ መዝገብ በአሸባሪነት ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ቃልም ማድመጥ ጀምሯል ። ዛሬ የአንዱን ተከሳሽ ቃል ያደመጠው ችሎቱ የተቀሩትን 18 ተከሳሾች የተከሳሽነት ቃል ለማዳመጥ ለነገ ቀጠሮ ሰጥቷል ። ችሎቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘገባ ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ