1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጽሃፍ አዉደ-ርዕይ በላይፕዚኽ

ረቡዕ፣ መጋቢት 10 2000

በአለማችን አንጋፋ የተባለዉ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ እዚህ በጀርመን በላይፕዚክ ከተማ በደመቀ ስነ-ስርአት ተከፍቶአል። የዚህ የመጽሃፍ አዉደ- ርዕይ ታሪክ ከአስራ ሰባተኛዉ ክፍለ ዘመን የጀመረ እንደሆን ምሁራን ይገልጻሉ። ማንበብን ባህሉ ያደረገዉ የጀርመን ህዝብም የሰዉ ልጅ ማንበብን ባህሉ ለማድረግ በ4 አመት እድሜዉ መስኮቱ ይከፈታል። እስከ ሰባተኛ እድሜዉ የማንበብን ባህል በዉስጡ ካልዳበረ ለባህሉ የተከፈተዉ መስኮት ይዘጋል የሚል አነጋገር አላቸዉ። ለ

https://p.dw.com/p/E0ll
በመጽሃፍ ትርኢቱ አዳራሽ
በመጽሃፍ ትርኢቱ አዳራሽምስል picture-alliance/ ZB

ዚህም ይመስላል ወላጆች ለልጆቻቸዉ በየአጋጣሚዉ የተለያየ መጽሃፍ በመግዛት ማራኪ ታሪክን በማንበብ የማንበብ ልምድ እንዲያድርባቸዉ የሚያደርጉት።

በአለም ታላቅ የተባለዉ የመጸሀፍ ትርኢት በምስራቃዊቷ ጀርመን በላይፕሲክ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ሲከፈት የኔደርላንዱ አሳታሚ Geert Mak አዉሮጻዉያንን ይበልጥ በማቀራረብ ረገድ ላቅ ያለ አስተዋጽኦ ላደረጉ የሚሰጠዉን የመጽሃፍ ትርኢቱን ሽልማት አግኝተዋል። ለአራት ቀናት የተካሄደዉ ይህ የመጽሃፍ አዉደ ርዕይ ከ40 አገሮች የተዉጣጡ 3000 ሺ ያህል የተለያዩ መጻህፍት አሳታሚ ድርጅቶች ደራሲዎች፣ የመጽሃፍ አቅራቢ ድርጅቶች ተሳታፊዎች ሆነዋል። ምስራቃ ምዕራብ ጀርመን ከተቀላቀሉ ወዲህ እንደ እ.አ 1991 አ.ም እንደ አዲስ የመጽሃፍ ትርኢቱን ለአለም ማሳየት ጀመረዉ የላይፕሲኩ የመጽሃፍ ትርኢት በአሁኑ ወቅት በመካከለኛዉ ምዕራብ አዉሮጻ አገሮች ያሉ ወጣት ደራስያን ባህላዊ ትስስር እንዲያደርጉ ታላቅ ድልድይም ሆንዋል። ይህ ዘመናዊ የመጽሃፍ ትርኢት ታድያ ባህላዊ የሆነ መሰረት እንዳለዉ ጀርመናዉያን በኩራት ይገልጻሉ። የዛሪዉ የባህል መድረካችን ይቃኘዋል ያድምጡ