1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጸዳጃ ስፍራ እጦት ከት/ት ገበታ ሲያስቀር

ዓርብ፣ ሐምሌ 28 2009

በኢትዮጵያ በተለይ በገጠራማው አካባቢ አሁንም ድረስ ከፍተኛ የአካባቢ ጽዳት ጉድለት እና የግል ንፅህና ችግር ይስተዋላል። ይህ ችግር በርካታ ልጃገረዶች ጭራሽ ትምህርት ቤት እንዳይሄዱ ያደረገበት አጋጣሚ እንዳለ የዛሬው የወጣቶች ዓለም እንግዳችን ገልጾልናል።

https://p.dw.com/p/2hglb
Benti Ejeta, COWASH, Äthiopien
ምስል B. Ejeta

በንቲ ኤጄታ የፊንላንድ እና የኢትዮጵያ መንግሥት በትብብር የሚሰሩበት COWASH በተባለ ድርጅት ባልደረባ ነዉ። ድርጅቱ ከሚያከናዉናቸዉ ተግባራት ዋናዉ  የንፁህ ውኃ አቅርቦት ፣ የአካባቢ እና የግል ንፅህና አገልግሎት ላይ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ በአምስት ክልሎች በሚገኙ 76 ወረዳዎች  ይሰራል።

Benti Ejeta, COWASH, Äthiopien
በንቲ ኤጄታ ምስል B. Ejeta

በንቲ በዚህ መርኃ ግብር ስር  ሲሰራ አምስት አመት ተቆጥረዋል። ወደዚህ ስራ ከመግባቱ በፊት በጋዜጠኝነት ሙያ የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ድርጅት ተብሎ ይጠራ በነበረው በንቲ ኢትዮጵያን እየተዘዋወረ ስላለው ችግር በታዘበበት እና በዘገበበት ወቅት የደረሰበት ድምዳሜ ገና ብዙ መሰራት እንዳለበት ነው። በተለይ  ወጣት ሴት ተማሪዎች  የወር አበባ ሲታያቸው በውሃ እና በመፀዳጃ ቦታ ማጣት ምክንያት ተማሪዎች በወር ለአራት ቀን በትንሹ ከትምህርት ቤት እንደሚቀሩ እና ትምህርታቸውን በአግባቡ መከታተል እንደማይችሉ በንቲ ይናገራል። ስለሆነም ሴቶች የመርኃ ግብሩ  ዋና ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ያስረዳል።

በንቲ COWASH  በሚሰራባቸው ሀገራት በሙሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ዓመት ባካሄደው አንድ ውድድር ላይ ተሳትፎ «የ ቶን ሻውትን» ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል። በተለይ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢ የንፁህ ውኃ አቅርቦት፣ ሰዎች ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ላይ ከዚህ የበለጠ መሰራት አለበት የሚለው በንቲ ኤጄታ ስለሽልማቱ እና ስለ ስራው ገልጾልናል።

ዘገባውን በድምፅ ያገኙታል።

 ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ