የመጠን ያለፈ የአየር ንብረትና ለዉጡ
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 26 2003ማስታወቂያ
በተፈጥሮ ረገድ፤ አዉሮጳና ሰሜን አሜሪካ በበረዶ፤ አዉስትራሊያና ብራዚል በጎርፍ፤ ፊሊፒንስ ከባድ ዝናብ ባስከተለዉ የመሬት መንሸራተት አንድ ብሎ ሥራዉን ጀምሯል። በተለያዩ አካባቢዎች የምናስተዉለዉ ከመጠን ያለፈ የሚባለዉ የአየር ጠባይ ሁኔታ ዓለም ከሚነጋገርበት የአየር ንብረት ለዉጥ ጋ ግንኙነቱ ምን ያህል ነዉ። የአየር ጠባይ ትንበያን ለማመን የሚያዳግታቸዉ ወገኖች እንዳሉ ሁሉ የየዕለቷን ትንቢት ተንተርሰዉ የሚንቀሳቀሱም ሞልተዋል። ክረምት ከበጋ የአለባበስ ስልቱ በማይቀያየር አካባቢ ለሚኖረዉ ኅብረተሰብ ዕለታዊዉ የአየር ጠባይ ትንበያ ብዙም ባላስጨንቀዉ፤ ለአዉሮጳና መሰል አካባቢ ኗሪዎች ግን ዋጋዉ ትልቅ ነዉ። ኢትዮጵያ ዉስጥ በዚህ ረገድ ብዙ ብዙ ይባላል።
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ