የመጓጓዣ ችግር በአዲስ አባባ
ረቡዕ፣ ኅዳር 26 2005ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ፣ ቅጥ ያጣ ሆኗል የተባለው የታክሲ አገልግሎት ህዝቡን ማስመረሩ ተነገረ።
እንደከተማይቱ ኑዋሪዎች ገለጣ፤ ት/ቤትም ሆነ ቢሮ በሰዓቱ መድረስ አልተቻለም። ለተለያዩ ጉዳዮች በየዕለቱ በሚደረግ እንቅሥቃሤም ላይ እክል እየፈጠረ ነው። በዚህ ላይ ግፊያው ሽምግሌዎችን ለእንግልት ሲዳርግ ተስተውሏል። በታክሲ የሚመላለሱ ሰዎችን ችግር የታዘበው ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር ዘገባ ልኮልናል። በሌላ በኩል በተለያዩ አካባቢዎች የሚካሄደው የከተማ መንገድ ሥራና ቁፋሮ፤ የተሽከርካሪዎችን ፍጥነት መግታቱና መጨናነቅን ማስከተሉ ተመለከተ። በመሆኑም ፣ በጊዜ ካሰቡት ቦታ ለመድረስ አዳጋች እየሆነ ነው። ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ የህዝብ አስተያየት አሳባስቦ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ጌታቸው ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ