የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት 100ኛ ዓመት መታሰቢያ
እሑድ፣ ሐምሌ 27 2006ማስታወቂያ
ልክ በዛሬው ቀን እሁድ፣ እንደ እጎአ ሐምሌ 3 ቀን፣ 2014 ነበር ጀርመን በፈረንሳይ ላይ ጦርነት እንደምትከፍት ያወጀችው። ሁለቱ የጀርመን እና የፈረንሳይ ባለስልጣናት ዛሬ በምስራቅ ፈረንሳይ ሐርትማንስቫይለርኮፍ በሚባለው ቦታ ኤልሳስ ውስጥ ተገኝተው የመታሠቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል። እጎአ ከ1914 -1918 ዓም የ1ኛው የዓለም ጦርነት በተካሄደው ከባድ ውጊያ ወደ 30,000 የሚጠጉ የፈረንሳይ እና የጀርመን መታደሮች ሕይወት ጠፍቷል። በእዚህ የዛሬው የመታሰቢያ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙ 100 የፈረንሳይ እና የጀርመን ወጣቶች በዓለም ዙሪያ ዘረኝነትን እናጥፋ የሚል የሰላም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የጀርመኑ ፕሬዚዳንት በአበባ ጉንጉን ማኖሩ ስነ-ስርዓት ወቅት፤ «ሰው በላው» የተሰኘው ተራራ ጦርነቱ የተካሄደበት ዘመን ትርጉም አልባ እና አሰቃቂ ሁናቴን እንደሚያመላክቱ ጥቂት ቦታዎች ሁሉ ተምሳሌት ነው ብለዋል። የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት በበኩላቸው በስነ-ስርዓቱ ወቅት፤ «አውሮጳ ጦርነቱን ድል ለመንሳት ተሳክቶለታል» ሲሉ ተደምጠዋል።
የጀርመን እና የፈረንሳይ ዕርቀ-ሠላም እና ወዳጅነት ለበርካታ የዓለማችን ክፍሎች አብነት ሊሆን የሚችል ነው ተብሏል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ልደት አበበ