1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጀመሪያው ባለ ስዕል መጽሐፍ ቅዱስ

ዓርብ፣ ሐምሌ 2 2002

በዓለም የመጀመሪያው በስዕል ተደግፎ የተጻፈ መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮዽያ ተገኘ። መጽሐፍ ቅዱሱ የተገኘው በሰሜን ኢትዮዽያ በትግራይ ክልል አድዋ አከባቢ በሚገኘው የአባ ገሪማ ገዳም ውስጥ ነው።

https://p.dw.com/p/OF9f
ምስል AP

አቶ መሠረት ሃይለስላሴ በትግራይ ብሔራዊ ክልል ባህልና ቱሪዝም ኤጀንሲ የቅርስ ምዝገባ ባለሙያ እንደሚሉት ተገኘ የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ የነበረ በክልሉ ባህልና ቱሪዝም ኤጀንሲም ተመዝግቦ ያለ ነው። የአንግሎ ፍሬንች የቅርስ አጥኚ ቡድን ያደረገው መጽሐፍ ቅዱሱ ከዕድሜውና በውስጡ ከያዛቸው ነገሮች አንጻር በአፈታሪክ የሚነገረውን በሳይንሳዊ ጥናት ማረጋገጡ ነው ብለዋል-አቶ መሠረት። በቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም በአጥኚ ቡድኑ ውስጥ የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤትክርስቲያንን በመወከል የተሳተፉት መምህር ዳንኤል ሰይፈሚካዔል በበኩላቸው መጽሐፍ ቅዱሱ በቤተክርስቲያኒቱ በትውፊት መልክ ይነገሩ የነበሩትን ሳይንሱም ደግፈዋቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ