የመድኃኒት ጥራት ጥያቄ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 8 2009ማስታወቂያ
የዲላዉ ነዋሪ ጠያቂያችን ጥያቄያቸዉን በላኩበት በደብዳቤ እንደዘረዘሩልን፤ በተለያዩ ጊዜያት የገዟቸዉመድኃኒቶች የተጻፉበት የፊደል ዓይነት እና መጠን የተለያየ ነዉ፤ አንደኛዉ በትልቅ ሌላኛዉ በትንንሽ። ስማቸዉ አንድ ሆኖ ሳለ ያስከተሉት ዉጤት ግን ተለያይቶ እሳቸዉ በህመም ሊሰቃዩ ግድ ሆኖባቸዋል። የአንድ መድኃኒትን ትክክለኛነት እንዴት መለየት ይችላል? አቶ ዘላለም ዘሪሁን ፋርማሲስትነት ናቸዉ፤ እዚህ ጀርመን ሀገር በሙያቸዉ ያገለግላሉ። ስለመድኃኒቶች የፈዉስ አቅም እና የጥራት ልዩነት ከባለሙያ ማብራሪያ እንድናፈላልግ ከአንድ አድማጫችን ለቀረበልን ጥያቄ ጊዚያቸዉን ወስደዉ በዛሬዉ ዝግጅታችን ሙያዊ ማብራሪያቸዉን ሊሰጡን ፈቃደኛ ሆነዋል። አቶ ዘላለምን በቅድሚያ እስከ ኦሪጅናል ስለሚባሉትና ስላልሆኑት መድኃኒቶች አብራሩልን ብለናቸዋል።ከኢትዮትዮጵያም መድኃኒት ወደ ሀገር ስለሚገባበትና ገበያዉ ላይ ስለሚገኙ መድኃኒቶችም የሚመለከታቸዉን ለማነጋገር ጥረት ጀምረናል። ጤናችንን ለማግኘት ብለን የምንወስዳቸዉ መድኃኒቶች ጉዳይ ትኩረት ያሻዋልና።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ