1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመድረክ ወቀሳና የመንግሥት ማስተባበያ

ሐሙስ፣ ግንቦት 26 2002

መድረክ ይወቅሳል። መንግስት ያስተባብላል።

https://p.dw.com/p/Ngkp
ምስል DW

ሥምንት ፓርቲዎችን የሚያስተናብረዉ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ በሺ የሚቆጠሩ አባላትና ደጋፊዎቹን መንግሥት አሰራቸዉ በማለት ወቀሰ።የመድረክ ከፍተኛ ባለሥልጣን ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዳስታወቁት በተለያዩ ቦታ የሚገኙ የፓርቲዉ አባላትና ደጋሪዎች እየታሰሩ ነዉ።የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ግን ከምርጫዉ በሕዋላ የታሰረ የተቃዋሚ አባል የለም ብለዋል።የኢትዮጵያን ፖለቲከኞች ለማስታረቅ የሐገር ሽማግሌዎች ጣልቃ ገብተዋል መባሉን፥ ፕሮፌሰር መረራ «ሞክረዉ» ነበር ሲሉ፥ አቶ ሽመልስ ሽምግልና የሚያስፈልገዉ ነገር የለም ብለዋል።መሳይ መኮንን ሁለቱን ባለሥልጣናት አነጋግራቸዋል።

መሳይ መኮንን

ተክሌ የኋላ