የመኾኖ ነዋሪዎች አቤቱታና የአስተዳደሩ መልስ
ዓርብ፣ መጋቢት 27 2005ማስታወቂያ
የትግራይ ክልል የመሆኖ ወረዳ ነዋሪዎች ለአመታት የኖርንባቸውን ቤቶቻችንን እንድናፈርስ እየተደረገ ነው ሲሉ አማረሩ ። ነዋሪዎቹ ቤቶቹ ህጋዊ ናቸው ቢሉም የወረዳው መስተዳድር ግን በህገ ወጥ መንገድ መሰራታቸውን አስታውቋል ። የአካባቢው አስተዳደር ቤቶቹ የሚፈርሱት ለእርሻ የተሰጡና ለአዲስ ጎጆ ወጪዎች የተያዙ መሬቶች ተሸጠው በህገ ወጥ መንገድ ለቤት መሥሪያነት በመዋላቸው ነው ይላል ። ቤት በማፍረሱ ሂደት ወደ አካባቢው ለእርዳታ የተላከ አንድ ሰው ፣ ቤት ተደርምሶበት ህይወቱ ማለፉን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዘግቧል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ