በስቶክሆልም የመኪና ግጭት ጥቃት ቢያንስ ሦስት ሰዎች ተገደሉ
እሑድ፣ ሚያዝያ 1 2009ማስታወቂያ
አርብ ከቀትር በኋላ ስቶክሆልም ስዊድን ውስጥ በሚገኝ የገበያ ማዕከል በአነስተኛ የጭነት መኪና ሆነ ተብሎ በተፈፀመ ግጭት ቢያንስ የሦስት ሰዎች ህይወት ጠፋ ። በርካታ የንግድ መደብሮች በሚገኙበት እና ገበያተኞችም በሚንቀሳቀሱበት በዚሁ ቦታ በደረሰው አደጋ በርካቶችም መቁሰላቸውን ፖሊስ አስታውቋል። ጥቃቱ በደረሰበት አካባቢ የተኩስ ልዉዉጥ መሰማቱን የዓይን እማኞች ተናግረዋል ። አደጋው የሽብር ጥቃት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል ። ፖሊስ እስካሁን አንድ ተጠርጣሪ መያዙ ተገልጿል። ለጥቃቱ እስካሁን ማንም ኃላፊነት አልወሰደም። ከአደጋው በኋላ የምድር ውስጥ ባቡሮች አገልግሎት ተቋርጧል ። የከተማዋ ቲያትር እና ፊልም ቤቶች ተዘግተዋል። የአውሮጳ መንግሥታት ጥቃቱን በማውገዝ ለስዊድን ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል።
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ